የስደተኞች ከፍተኛው ፍራቻ በአውስትርያ የሚገኘው የቀኝ ክንፍ ሕብረትን ነው
ፎቶ የመዘገበ፡ ሰባስቲያን ኩርዝ © ቢቢሲ 2017
እ.አ.ኣ ጥቅምት 15 ሰባስቲያን ኩርዝ የሚመራው የአውስትርያው ወግ አጥባቂው ህዝባዊ ፓርቲ የአገሪቱ ጠቅላላ ምርጫ በአውስትርያ ካለው የግራ ክንፉ የሶሺያል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ከ30% በላይ በሆነ ድምፅ አሸንፏል፡፡
ምርጫው ያሳየው ከግማሽ በላይ የሆኑት የአገሪቱ መራጮች በፀረ-ስደትና የስደተኞች መብት ላይ ዘመቻ ያካሄዱት ፓርቲዎችን መደገፋቸው ነው፡፡ የቀኝ ክንፉ ማለት የፀረ ስደተኞች ፈሪደም ፓርቲ የምርጫው 27% በማግኘት ሦስተኛ ሆኗል፡፡
ምንም እንኳ ኩርዝ ስደትን በሚመለከት ከሌሎች ፓርቲዎች ሻል ያለ አቋም ቢኖራቸውም ቅሉ፣ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ግን የሽንገላ ፅሁፍ/ሃሳብ በማቅረብ ረገድ ከፍሪደም ፓርቲ ጋር ተመሳሳይነት እንዳላቸው ተገንዝበዋል፤ ይኸውም ከአደጋ የዳኑትን ስደተኞች ወደመጡበት አፍሪካ መልሶ በመላክና አዲስ ለሚመጡት ስደተኞች አንዳንድ ጥቅሞችን በሰፊው በመቁረጥ ረገድ ነው፡፡
አብላጫው የአውስትርያው ወግ አጥባቂው ህዝባዊ ፓርቲ ከፈሪደም ፓርቲ ጋር የኅብረት መንግሥት እንዲመሠርት ይጠበቃል፡፡ ይኸውም ስደተኞችንና የሙዝሊም ማኅበረሰብን እንደዚሁም ንቁ የፖለቲካ ሰዎችንና የቀኝ ክንፎችን የሚያሳስብ ሁኔታ ነው፡፡
ዘካርያ አብርሃም የተባለ ስደተኛ ለቫይስ ዜና ሲናገር፣ “ከሁለት ዓመት በፊት ወደ አውስትርያ ስመጣ፣ የአውስትርያ ሕዝብ እንደኔ ያሉት ስደተኞችን ሲቀበል በጣም አመሰግነው ነበር፤ በኋላ ግን ቀስ በቀስ ብዙ ነገር ተለውጧል፣ ማለት በአጠገቤ ያለው የአውስትርያ ኅብረተሰብ በስደተኞች ላይ አሉታዊና የጥላቻ ስሜት እንዳለው ተገንዝቢያለሁ፡፡”
የአውስትርያ መንግሥት በፀረ ስደተኞች ፓርቲ ስለሚመራና በዚሁ ምክንያትም ያለው ፍራቻ በተጨማሪ ሲገልፅ፣ “እኔ የሚያሳስበኝ ይህ የፍሪደም ፓርቲ እንደ መንግሥት አገሪቱን መምራት ሲያቆም እኛ ስደተኞች ምን እንደምንሆን ነው፡፡ የቀኝ ክንፉ ፓርቲም ስደተኞችን ከአውስትርያ እንደሚያባርር ቃል ገብቷል፡፡”
በአውስትርያ ፖለቲካ ይህ ስደተኞችን ወደ ጎን መተው አዝማሚያ የመጣው በመላው አውሮፓ የፀረ ስደተኞች ስሜት ጎልቶ በመውጣቱና የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻዎች በአህጉሩ እየበዛ በመምጣቱ ነው፡፡ በቅርቡ ዓመታት አስር ሺ የሚሆኑ ስደተኞች በውስትርያ ብቻ ሰፍረዋል፡
በሚቀጥለው ምርጫ ቻንስለር ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ኩርዝ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በነበሩበት ወቅት በባልካን አካባቢ የአውስትርያ ጠረፍ በመዝጋት የስደተኞች ፍልሰት አቁመውት እንደነበር አጉልተው ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም አውሮፓ የሳቸውን መንገድ ተከትለው ስደተኞች ወደ አህጉሩ የሚገቡበት ዋናው መንገድ የሜዲቴራንያን ማስተላለፊያ መንገድ መዝጋት እንደለባቸው አሳስበዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ