የኢጣልያ ፖሊስ ህገወጥ የሠዉ አዘዋዋሪ ቡድኖችን መረብ በጣጠሰ
አጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ከሆነ የጣልያን ፖሊስ በግብፃዉያን ሱዳናውያን፣ ምስራቅ አዉሮፓውያንና
ጣልያናዉያን የሚመራዉን በህገወጥ የሰዉ ንግድ ላይ የተሰማሩ ቡድኖችን ከጥቅም ዉጭ አድርጓል፡፡
የጣልያን ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ከሆነ እነዚህ በጥር 30፡ 2017 በቁጥጥር ስር የዋሉ 13 ህገወጥ አዘዋዋሪዎች
ለሁለት ዓመታት ያካሄደዉ ጠንካራ ክትትል ዉጤት ነዉ፡፡ ይህ በህገወጥ የሠዉ ንግድ ላይ የተሰማራዉ መረብ አዉሮፓ
ዉስጥ የሚካሄደዉን አደገኛ የህገወጥ የሠዉ ንግድ ማዘዋዋር ላይ ተሰማርቶ የቆየ ነዉ፡፡
ይህ በሚላን ከተማ ዉስጥ መቀመጫዉን በማድረግ ከህገወጥ ስደተኞች በርካታ ገንዘብ በመሰብሰብ ሲሰራ የቆየ
ቡድን ህገወጥ ስደተኞችን ድንበር በማሻገር ለአካላዊ ጉዳትና ኢሰብአዊ አያያዝ ሲደርጋቸዉ የነበረ ነዉ፡፡
የኢጣልያ ፖሊስ ለሁለት ዓመታት እነዚህ ወንጀለኛ ቡድኖች ሲጠቀምባቸዉ የነበሩት 62 የህገወጥ የስዎች ማዘዋወሪ
መስመሮችን ለማግኘትና ለመቆጣጠር ያደረገዉ ስኬትማ ክትትል ነዉም ተብሏል፡፡
እንደተባበሩት መንግስታት የዕፅና የወንጀል መከላከል ድርጅት (UNODC) መረጃ እነዚህ በህገወጥ የሠዉ ንግድ ላይ
የተሰማሩ ቡድኖች ከአፍሪካ ወደ አዉሮፓ ህገወጥ ስደተኞችን በማዘዋወር እስከ 150 ሚሊዩን ዶላር ሰብስበዋል፡፡
ህገወጥ ስደተኞች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወሩም በየሃገሩ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉም ብሏል፡፡
የህገወጥ ቡድኖቹ በቁጥጥር ስር መዋል ለኢጣልያ ባለስልጣናት ወንጀለኛ ቡድኖችን ለማጥፋት በሚያደርጉት ጥረት ላይ
ትልቅ እምርታ ነዉ ተብሏል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ