የሊቢያ የባህር ክልል ጠባቂዎች አራት ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ገደሉ

TMP – 23/04/2017

የሊቢያ የባህር ክልል ጠናቂዎች ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ጋር በሚያዚያ 6 ከባድ የተኩስ ልውውጥ ያካሄዱ ሲሆን፤ በተኩስ ልውውጡ አራት መገደላቸውን የጠባቂዎቹ ቃለ አቀባይ ኣዩብ ቃሲም ገልጸዋል፡፡

ግጭቱ የተጀመረው የባህር ክልል ጠባቂዎች ከባድ የጦር መሳሪያ የታጠቁትን አዘዋዋሪዎች ለመያዝ ሲሞክሩ መሆኑን የገለጹት ቃል አቀባዩ ጀልባቸውም ኮትሪፓሊ 45 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዛውያ ከተማ በነበረችው የስደተኞች ጀልባ አጠገብ ነዉ፡፡

የባህር ጠባቂዎቹ የታጠቁ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን የጫነች ጀልባን በራዳር እንደተመለከቱ ገልጸው ባሉበት እንዲቆሙ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ስደተኞች የያዙ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች መሆናቸው በመታወቁ ነውም ብለዋል፡፡ ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ጥያቄውን በመንፈግ ተኩስ መክፈት ሲጀምሩ የመልስ ተኩስ ከባህር ጠባቂዎች መካሄዱም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት አራት ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተገድለው ሁለት በቁጥጥር ሲውሉ አንድ እንደተሰወረም ገልጸዋል፡፡ አንድ ከባህር ጠባቂዎች ጋር የነበረ ጀርመናዊ ጋዜጠኛም በቀላሉ ቆስሏል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ጥር 23 የሊብያ የባህር ክልል ጠባቂዎችን ለማጠናከር የስልጠናና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረጉ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን የመግታትና የመቆጣጠር አቅሙ እያጠናከረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡