ሃንጋሪ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በኮንቴይነር ልታሰፍር ነው

TMP – 23/04/2017
ሃንጋሪ ወደ አገሯ ለሚገቡ ስድተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን በድምበር ባሉ ከኮንቴይነሮች በተሰሩ ቤቶች ልታሰፍር እንደተዘጋጀት ታውቋል፡፡

ከመጋቢት 28 ጀምሮ በሚተገበረው ሕግ መሰረት ሁሉም ስደተኞች ከሰርቢያ ድንበር አቅራብያ ይቆያሉ፡፡ ወደ ድንበርዋ ለሚመጡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ከ14 ዓመት በላይ ለሆኑ ህፃናት ጭምር ለመኖርያ በተዘጋጀው ኮንቴይነሮች ይቆያሉ፤ ይህም የጥገኝነት ማመልከቻቸው ሂደቱን እስኪጨረሱ ድረስ እዛው እንዲቆዩና ለመታገታቸውም ምንም አይነት ቅሬታ ማቅረብ እንደማችሉ ታውቋል፡፡

በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር የተሰጠው መግለጫ አዲሱን እርምጃ እንደሚገልፀው “የዚህ እርምጃ ዋና አላማ ሁኔታቸው ያልታወቀ ስድተኞች በሃገሪቱ ግዛትና በአውሮፓ ሕብረት በነፃ እንዳይዘዋወሩ ለመገደብና የድህንነት ስጋትን ለመቀነስ ነው፡፡ ማነኛውም ህገ-ወጥ ስድተኛ በአገር ውስጥ የተያዘ ወደ ድንበር ተመልሶ ይሸኛል፡” ሲል መግለጫው ይቀጥላል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር ቪክቶር ኦርባን ደጋግመው እንዳሉት “ጥገኝነት ጠያቂዎች ላልተወሰኑ ጊዝያት አይደለም የሚታሰሩት፤ በማነኛውም ግዜ ወደ ሰርብያ ለመጓዝ ሊመርጡ ይችላሉ፡፡”

ይህን ጠንካራ ሕግ በሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ቡድንና በተባበሩት መንግስታት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ነገር ግን የሃገሪቱ መንግስት እርምጃው ከድህንነት ጋር በማያያዝ ተከላክሏል፡፡ የአውሮፓ ኮምሽን የማቆያ ስፍራዎችን እንዲመረመሩ እንዲጎበኝ እቅድ እንዳለውና ለስደተኞች ምቹ ሁኔታዎች መሟላታቸውና የአውሮፓ ሕብረት መመዘኛዎች ያሟሉ መሆናቸው ያረጋግጣል፡፡

ሊድያ ጋል የተባለች የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ቡዱን ተመራማሪ እንዳለችው “በሃንጋሪ በቅርቡ የወጣው ሕግና ፖሊሲ ሕገ ወጥና ለተገን ጠያቂዎች አስቸጋሪና የማያስደስት ወይም እጅግ አደገኛ ነው፡፡” ሃንጋሪ ለዚህ ጠንካራ ሕግ የሰላ ትችት ለስድተኞች አያያዝዋ ከ 2015 ጀምሮ ቢገጥማትም ጠቅላይ ሚኒስተር ኦርባን ግን በስድተኞች አያያዝዋ ለሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ጥሩ ምሳሌ እንደሆነች ይናገራሉ፡፡

ሃንጋሪ ከ 1745 የጥገኝነት ጥያቄዎች በዚህ ዓመት 34 ስደተኞች ብቻ ተቀብላለች። በ2017 ሁለት ወራት ውስጥ ወደ 7000 የሚሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች በሰርቢያ ድንበር እንደሚገኙና በየቀኑ ወደ ደርዘን የሚጠጉ ብቻ ወደ ሃንጋሪ እንዲገቡ እንደሚፈቅድላ