የእሳት ቃጠሎ የዳንኪርክ አቅራብያ የሚገኘው የስደተኞች መኖርያ አወደመ

TMP – 22/04/2017
ሓይለኛ የእሳት ቃጠሎ በሰሜናዊቷ ፈረንሳይ ከተማ ዳንኪርክ የሚገኘው ታላቁ የስደተኞች መኖርያ ካምፕን ባለፈው ሰኞ ሚያዝያ 10 እንዳወደመው ታውቋል፡፡

ከቃጥለው የሚወጣው ጭስ በብዙ ማይሎች ርቀት ሆኖ በጥቁሩ ሰማይ ላይ ይታይ እንደነበርና እሳቱ እስከ ማክሰኞ ማለዳ ድረስ እንደቀጠለ ታውቋል፡፡ ካምፑ ከ1000 እስከ 1500 ስደተኞች ከእንጨት በተሰሩ ትናንሽ ጎጆዎች ይኖሩባቸው እንደነቡሩና ሙሉ ለሙሉ እንደወደሙና ወደ 10 የሚሆኑ መለስተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስድተኞች ወደ አቅራብያው ሆስፒታሎች እንደተወሰዱ ታውቋል፡፡

የአካባቢው ሃላፊ ሚሸል ላላንድ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ምንም የቀረ ነገር የለም የአመድ ክምር ካልሆነ በስተቀር የመኖርያ ጎጀዎቹን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የማይቻል ነገር ነው፡” ሲሉ አክለው ገልፀዋል ዘገባው እንደሚያመለክተው እሳት ቃጠሎው የተነሳው በኣፍጋንያንና ኩርዶች ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ብጥብጥ ሁከት መሆኑና ብጥብጡ ወደ ሌላ የባሰ ደረጃ እንዳይደርስ የፖሊስ ሃይል ጣልቃ ገብቷል፡

የአካባቢው ሓላፊ አሊቪየር ኣራሜል እንዳለው “በግጭቱ ወቅት ሆን ተብሎ በእሳት የማቃጠል ስራ በተለያዩ ቦታዎች እንደተደረጉ ካልሆነ እሳቱ ዝም ብሎ ሊነሳ ኣይችልም። አብዛኛዎቹ ጎጆዎች ተቃጥለዋል ወይም እየተቃጠሉ ነው፡፡ የካምፑ  ግማሽ በሙሉ ወድሟል።” በጉዳቱ ለተፈናቀሉ ስደተኞች ሌላ አማራጭ ማቆያ በአካባቢው ጅምናዝየሞች ተሰጥቷቸዋል፡፡

የፈረንሳይ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ብሩኖ ለሩ ባለፈው ወር የስድተኞቹ ካምፕ እንደሚዘጋ አስታውቀው ነበር፡፡ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኝ የነበረው የ ካሌ የስደተኞች መጠለያ በእሳት ቃጠሎ ከወደመና ከተዘጋ ወዲህ በዚሁ የስደተኞች መጠልያ ጣብያ ቁጥራቸው ከ700 ወደ 1500 ገደማ እንደጨመረ ታውቋል፡፡

የእሳት ቃጠሎው ተከትሎ በቅርብ ወራቶች በግራን-ሲንት ካምፕ የተለያዩ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ በመጋቢት ወር 5 ሰዎች በድብደባ ከተጎዱ በኋላ ፖሊስ ጣልቃ መግባቱና በህዳር ወር ደግሞ ሌላ አንድ ሰው በስለት መውጋቱ ይታወቃል፡፡