በመካከለኛው ባህር የሚይሳጋጥም ይስደተኞት ሞት ከፍተኛ ቁጥር ደሰዋል

በ2016 በማካከለኛው ባህርና በአውሮፓ በኩል ድንበር ሲሻገሩ የሞቱ ስደተኞች ቁጥ ከ5,000 /አምስት ሺ/ በላይ ሆኖዋል፡፡ ከአውሮፓ ድንበር ሊሻገሩ የቻሉ ስደተኞች ቁጥር ሲወዳደር፤ በተለይ ከቱርክ ወደ ግሪክ የሚያሻግር መስመር ከመዘጋቱ  በሃላ፤ በምስራቃዊ መካከለኛ ባህር በ 2/3ኛ ቀንሰዋል፡፡

የሙታን ቁጥር 5,000/አምስት ሺ/ የደረሰው በ 22 ታህሳስ በኢጣልያ ባህር ዳርቻ በሁለት ጃልባ ከተሳፈሩ 257  ተሳፋሪዎች 100 /አንድ መቶ/ የሚያህሉ እንኳን ለማዳን አልተቻለም፡፡

የተባበሩት አገራት ድርጅት ቃል አቀባይ የበላይ ኮሚሽነር ስለ አስከፊና አሰቃቂው አደጋ በተናገሩበት ግዘ፤ ይህ ቁጥር በ 2016 እ.አ.አ በአውሮፓ የተሻለ ህይወት ለማግኘት ሲሉ በሁሎም ድንበሮች በየቀኑ 14 ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተባበሩት አገሮች ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተል ቅንጫፍ በሰጠው መግለጫ መሰረት፤ ድንበር አሻጋሪዎች የሚጠቅምባቸው የጃልባው ዓይነት እየባሰ ከመሄዱ በተጨማሪ፤በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ የሚከተሉትን ሜላ በይበልጥ በተራቀቀ መንገድ እንዲሆን እያደረጉት መሆናቸው ታይተዋል፡፡ በ2016 አሻጋሪዎች በአንድ ግዜ በጣም ቡዙ ጃልባዎች በመላክ ከመያዝ እንዲያመልጡ የሚከተሉት ሜላ ወይም ብልሃት ለህይወት መዳን እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እንዲሆን ስለ አባባሰ ኣብዛኞቹ ስደተኞች እርዳታ ማግኘት ባለመቻላቸው አልቀዋል፡፡

በመካከለኛው ባህር ከፍተኛ የሟች ሰዎች ቁጥር ጨምረዋል፡፡ ይህ ወደ አውሮፓ ሊደርሱ የሚችሉ ስደተኞች ቁጥር በቀነሰበት አመት የሚያጋጥም ነው፡፡ በአህጉራዊ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ በሰጠው መረጃ መሰረት፤ በ 2015፡ 1,000,000 /አንድ ሚልዮን/ የሚያህሉ ስደተኞች የአውሮፓ ድምበር ሲረግጡ፤ በ 2016 ይህ ቁጥር ከ 360000 /ሰዎስት መቶ ስልሳ ሺ/ በታች ወርድዋል፡፡

ወደ አውሮፓ ከሚጎርፉ የስደተኞች መጠን ሲታይ፤ በ 2016 በመካከለኛ ባህር የሞቱ የስደተኞች ቁጥር ከ 1/3 በላይ ጨምረዋል፡፡ በ 2015 ከ 3,770 ስደተኞች በላይ በባህር ውስጥ ጠፍተዋል፡፡ በ 2014 ደግሞ 3,280 የሚያህሉ ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከ 2016 በፊት ከነበረ የስደተኞች ከፍተኛ መጉረፍ  ከሞቱት ቁጥር ሲወዳደር፤ በ2016 የነበረ ባህር ላይ የሞት አጋጣሚ በሰዎስት ኢጅ ጨምረዋል፡፡