የኣውሮፓ ሕብረት በሊብያ ስድተኞችን ድህንነት ለመከላከል 90 ሚልዮን ዩሮ መደበ
የአውሮጳ ሕብረት በትራስት ፈንድ ለአፍሪቃ በኩል ስደተኞች ለመከላከልና የስድተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የስድተኞች አስተዳደር ለማጠናከር ዘጠና ሚልዮ ዩሮ መድቧል፡፡
የአውሮጳ ሕብረት ከፍትኛ ተወካይ ፈደሪካ ሞገሪኒ እንዳሉት “ሊብያና ሊብያውያን የአውሮጳ ህብረት ቅድሚያ ከሚሰጠቸው ጉዳዮች አንዱ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡ በሊብያ ለተከሰተው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመሻትና ለሊብያ ባለስልጣናት ለሚያጋጥሙኣቸው ተግዳሮቶች የስደተኞች ፍልሰትን ጨምሮ ለማገዝ ነው፡” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ 90 ሚልዮን ዩሮ ዛሬ ያፀደቅነው የስደተኞች ድህንነት ለመጠበቅና ስደተኞችን ለሚቀበሉዋቸውና ለሚያስተናግድዋቸው እርዳታ የሚውል ነው፡፡ የኛ አላማ በሊብያ የስደተኞችን ህይወት መታደግና በሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን መስራት ነው፡፡ የአውሮጳ ሕብረት የሚፈለግበት ድርሻው እየተወጣ ነው፡፡ የሊብያ ባለስልጣናት ደግሞ የድርሻቸው ማበርከት አለባቸው፥” ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ሞገሪኒ ጨምረው እንደገለፁት “የአውሮጳ ህብረት እስከ አሁን በእርዳታ ፓኬጅ መልክ ለመደገፍ 120 ሚልዮን ዩሮ እንደመደበና ተጨማሪ የስልጠናና የአቅም ግንባታ ለሊብያ የድንበር ጠባቂዎች ይህም በመወዲተራንያን ባህር የስደተኞች ህይወት ማዳን ለሚያደርጉት ስራ ለማገዝ መሆኑ ነው።”
አዲሱ ፕሮግራም የተለያዩ ሊብያና በማእከላዊ ሜዲተራንያን መተላለፍያ ዞን ለሚያጋጥሟት ችግሮች ለመቅረፍ ነው፡፡ ይህም የስድተኞችን ደህንነት መጠበቅና የስደተኞችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣ ለሚያስተናግዱዋቸው ህዝቦች እንዲሁም የውስጥ ተፈናቃዮችን ይጨምራል፡፡ ከሊብያ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ፍቃደኛ ለሆኑትም ድጋፍ ይደረጋል፡፡
ይህም ተግባራዊ የሚሆነው በዋና የስፍራ አከባቢዎችና መተላለፍያ በሮች ለምሳሌ በደቡባዊ የሊብያ ድንበር፣ ማዛጋጃ ቤቶችና የስደተኞች ምንጭ የሆኑትን አከባቢዎች እንዲሁም በድንበር አቅራቢያና የሊብያ ተፈናቃዮች ባሉባቸው አካባቢዎች የሊብያ ተፈናቃዮች የሚመለሱባቸው አካባቢዎችን ይጨምራል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ