የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ ግንኙነት የመፍጠር እቅድ ይዟል

አውሮፓ ህብረት ኮሚሽን – ህገወጥ ስደትን፣ የስራ ፈጠራ፣ ሰላምና ጸጥታን የሚመለከቱ ጉዳዮች ለመፍታት ከአፍሪካ ጠንካራና ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል አዲስ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

ይህ አዲስ ሁለንተናዊ ተግባር ባለፈው ህዳር ወር የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ ላይ በአፍሪካውያን ወጣቶች ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት የተደረሰው ስምምነት ቀጣይ ስራ ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ፈደሪካ ሞገሪኒ ‹‹ጠንካራ የሆነ አፍሪካና ይህን መሰረት አድርጎ የምንፈጥረው ትብብር ለኛም ሆነ ለህዝባችን ወሳኝ ጉዳይ ነው ካሉ በኃላ ሃይላችንን በማስተባበር የምንተገብረው ትብብር ወጣቶች ቀጣይ ዕድላቸው ሰላማዊና ተስፋ ሰጪ እንዲሆን ያስችላቸዋል ካሉ በኃላ ዛሬ ለአፍሪካ በምናደርገው ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ጋር በጋራ በመተባበር በምንሰራው ጉዳይ ላይ ነው ያነጣጠርነው ብለዋል፡፡

የህብረቱ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽነር ነቨን ሚሚካ በበኩላቸው “በቀጣይ በምናከናውናቸው ተግባራት ላይ በተለይም ለአፍሪካ ወጣቶች የስራ ፈጠራና ልማት ለመተግበር የሚያስችሉ የተለያዩ ተጨባጭ የሆኑ ሀሳቦችን በማቀድ ላይ ተስማምተናል” ብለዋል።

ዕቅዱ በአፍሪካ ቀጣይና ሁለንተናዊ የልማት ስራ በማከናወን በተለይ ለአሁጉሪቱ ወጣቶችን ስራ ፈጠራ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ይህ አፍሪካ ውስጥ የቴክኖሎጂ እድገትን እውን የሚያደርግ ዲጂታል ፎር ዲቨሎፕመንት ስኪም የተባለ መርሃ ግብርን ያካትታል፡፡