በባህር ከሚቶቱት ስድተኞች በበርሃ ውስጥ የሚሞቱት ይበዛሉ
ከሰሜናዊው ኒጀር በረሃ ወደ ሊብያ ሲጓዙ ከነበሩት ስድተኞች ይጓዙበት የነበረው መኪና በመበላሸቱ ቢያንስ 44 ስደተኞች በውሃ ጥም እንደሞቱ ታውቋል፡፡
የቀይ መስቀል ቃል አቀባይ እንደገለፀው በህይወት ከተረፉት 6 ሰዎች፡ ሁሉም ሴቶች፡ ወደ አንድ መንደር እንደተጓዙና ወደ 44 የሚጠጉ ሰዎች፡ ሶስት ህፃናትና ሁለት ልጆች ጨምሮ፡ በውሃ ጥም እንደሞቱ አስታውቋል፡፡
ቀይ መስቀል ስለጉዳዩ መረጃ ለመሰብሰብ አንድ ቡድን ወደ ቦታው እንዳሳማራ ታውቋል፡፡ ከምዕራብ አፍሪቃ ለሚሰደዱ ሰዎች ዋና መነሻ እና መናሃርያ የሆነችውና የኒጀር ከተማ አጋዴዝ ከንቲባ ረሂሳ ፌልቱ እንዳረጋገጡት በበረሃው የሞቱት ስድተኞች ቁጥር በአሁኑ ግዜ 44 ደርሷል፡፡ ይህ የተለየ አጋጣሚ አይደለም፤ 8 ስደተኞች ከኒጀር፡ ከነዚህም አምስቱ ህፃናት፡ በበረሃው ወደ አልጀርያ ሲያቀኑ ሞተው እንደተገኙና በአከባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩ ወታደሮችም 40 የሚሆኑ በህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በበረሃው ተጥለው የተገኙ ስደተኞች ህይወት እንደታደጉ ታውቋል፡፡
በጉዞው ወደ አውሮፓ በጣም አስቃቂ ከሆኑ የጉዞ ቦታዎች አንዱ በሆነው ስደተኘች በፒክ አፕ መኪኖች ታጭቀው በቀናት ጉዞ ከኒጀር ወደ ሊብያ በጣም ጥቂት ሊትሮች ውሃ ለማስያዝ የሚያስችል ቦታ ብቻ በሚቀረው ቦታ ተጠቅጥቀው እንደሚሄዱ ይታወቃል፡፡
ባለስልጣናትና የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች የሟቾች ቁጥር ለማወቅ ቢሞክሩም በሺዎች የሚቆጠሩ ሟቾች በአውሮፓና አፍሪቃ መካከል ያለው በሜዲትራንያን ባህር የሚሞቱት ቁጥር ለማወቅ እንደማይቻል ገልፀዋል፡፡
ባለፈው ዓመት የቀረበው የዴንማርክ ስደተኞች ካውንስል እንደሚያመለክተው ብዙ ስደተኞች በበረሃ እንደሚሞቱ ታውቋል፡፡
በአፍሪቃ ቀንድ ወደ ሊብያ፣ ግብፅና አውሮፓ ስድተኞችና በመጠሊያ የሚገኙ ስደተኞች በተከታታይ እንደሚያሳዩት ሜዲተራንያን ባህርን ሲያቋርጡ ከሚሞቱት በሰሃራ በረሃ የሚሞቱት ስድተኞች እንደሚበዙ ቢታወቅም ሓቀኛ የሟቾች ቁጥር ግን እስከሁን አልተገኘም ሲል ዘገባው ያመለክታል፡፡
የመድሃኒት አቅርቦት ማነስና ረሃብ ተደማምረው እንዲሁም የመኪኖች አደጋና በጥይት በቢላዋ ተወግተው የሚሞቱት መሆናቸው ዘገባው ያመለክታል።
ፅሑፉን ያካፍሉ