በዚህ አዲስ አመት 2018 በ10 ቀናት በሜድተራንያን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ 192 ስደተኞች እንደሞቱ ታወቀ
ስእል ሲ.ቢ.ሲ – በመዲትራንያን ባህር በመስመጥ ላይ ያለች ጀልባ
በአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ዘገባ መሰረት በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ስደተኞች ካፈው ጥር 6, 2018 የሚደተራንያን ባህርን ሲያቋርጡ የገቡበት እንዳልታወቀ /ድርሻቸው ወይም ደብዛቸው እንደጠፋ ታውቋል፡፡ ይህ ማለት በጥር ወር አጋማሽ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞች በማእከላዊው ሜድተራንያን ሞተዋል ወይም ደብዛቸው ጠፍተዋል፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ በዚህ አዲስ አመት ብቻ /8/ በስምንት ቀን ውስጥ 81/ ሰማንያ አንድ/ ሰዎች እንደ ሞቱ ሲታወቅ ይህም በጣልያን እና በሊቢያ ለሚደረገው ጉዞ መሆኑ ታወቋል፡፡
ጥር 9 ቀን በማእከላዊ ሜድተራንያን በተከሰተው ሁኔታ ሶስት የፕላስቲክ ጀልባዎች 279 ስደተኞች ከነዚህም 19 ሴቶች ሲሆኑ 243 ወንዶች እንዲሁም 17 ህፃናትን ጨምሮ በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ማዳን እንደተቻለ ታውቋል፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በተጎጆዎች ማቆያ ማእከል ተገኝቶ የምግብና የውሃ እርዳታ እንደኣደረገ ለማወቅ ተችለዋል፡፡ እንደ ተጎጅዎቹ ገለፃ ከሆነ ወደ 100 የሚጠጉ ስደተኞች ደብዛቸው እንደጠፋ ተናግረዋል፡፡
በለብያ የአለም አቀፍ ስድተኞች ጉዳይ ዋና ሓላፊና ተወካይ ኦትማን በልበሲ እንደሚሉት ከሆነ” ወደ 700 የሚጠጉ እንደዳኑና ብዙ ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ” ታውቋል፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የጠፉት ስደተኞች ፕሮጀክት እንደዘገበው በጥር 9¸2018 በምዕራባዊው ሜድተራንያን 43 ስደተኞች ከመስጠም ካመለጠው ጀልባ እነደዳኑ ታውቋል፡፡ የሶስት ሰዎች/3/ አስከሬን በጀልባዋ ውስጥ እንደተገዑም ታውቋል፡፡ ከሞት የዳኑት ሰዎች እንደገለፁት ከሆነ 8 ሰዎች እነደሞቱ ወይም ደብዛቸው እንደጠፋ ታውቋል፡፡ ባለፉት 11 ቀናት ብቻ የሟቶች ቁጥር በምዕራባዊው ሜድተራንያን 16 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡
እስካሁን ድረስ በዚህ የ ፈረንጆች አዲስ ዓመት ብቻ የሟቶች ቁጥር 192 መድረሱና ካለፈው ዓመት 2017 ጋር ሲነፃፀር 12 ሰው ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ