ጀርመን በኢትዮጵያ ለስደተኞች የስራ እድልና የስልጠና ፕሮግራም ልትከፍት ነው
በኢትዮጵ በስደት ለሚኖሩና የሚያስተናግዋቸው ማህበረሰብ አባላት በሚቀጥለው ጊዜ ታላቅ የክህሎት ማሳደግያና የስራ እድል ፈጠራ በአዲስ አበባ በሱማሌና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሩህ ተስፋ ሰንቀዋል:: ይህም ጀርመን የ4 ዓመት ስደተኞችን ከማህበረሰቦቻቸው ለማገናኘትና ለማቀላቀል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷና ማስታወቅዋ ተከትሎ መሆኑ ታውቋል::
አዲሱ የስልጠና መርሃ ግብርና የስራ ዕድል ፈጠራ ለስደተኞች ኢትዮጵያውያን በሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲቹሉና የትምህርትና የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው የትምህርት ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሳህለ ተካ ተናግረዋል::
በመክፈቻው ስነ–ስርዓት ጥቅምት 17 እ.ኤ.አ 2018 ተገኝተው ባሰሙት ንግግር አቶ ሳህለ ተካ እንደገለፁት ይህ ዓይነት ስልጠና መጀመርያ ትኩረት የሚያደርገው የስራ እድል ማሻሻል ላይ ሲሆን ይህም ለ1500 ከስደት ተመላሽ ዜጎችና የማህበረሰቡ አባላት መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ (ወጪ በማድረግ) የተግበር እድ ስለጠና በመስጠት መሆኑ ታውቋል::
ኣውሮጳ ለኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በማሰልጠን ለክህሎትና ለስራ እድል ፈጠራ መዋእለ ንዋይ (ገንዘብ) ስታፈስ ቆየታለች:: ብሪጣንያ ባለፈው ሰኔ ወር የ115 ሚልዮን ፓውንድ በጀት መፈረምዋ ይታወቃል:: ይህም በኢትዮጵያ ለታክስ ስርዓት ሪፎርምና የስራ እድል ፈጠራን ለማገዝ መሆኑ ታውቋል:: እንደ ማእከላዊ የስታቲስቲክስ መረጃ ኤጀንሲ ዘገባ ከሆነ በ2015 ዓ/ም እ.ኤ.አ የስራ አጥነት መጠን 16.8 በመቶ መሆኑ ታውቋል::
ኢትዮጵያ በ27 የስደተኞች መጠልያ ማእከላትና በ6 ክልሎች ወደ አንድ ሚልዮን ስደተኞችን እንደምታስተናግድና በአፍሪቃ ሁለተኛዋ አገር ስትሆን አብዛኛዎቹም የመጡት ከኤርትራ ፣ ከሱዳን ፣ ከደቡብ ሱዳን ፣ ከሶማልያና ከየመን መሆናቸው ታውቋል::
በሱማሌና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ወደ 320,000 ስደተኞች እንደሚገኙ በተ.መ.ድ የስደተኞች ኤጀንሲ ከፍተኛ ኮሚሽን ዘገባ ያስረዳል:: በአዲስ አበባ ደግሞ 22,000 የሚጠጉ የከተማ ስደተኞች እንዳሉ ሲታወቅ፡ የሃገሪቱ ሩብ ያክል ወጣቶችና ስራ አጦች ባሉበት ሃገር ትልቅ ጫና እንደሚሆን ዘገባው ያስረዳል::
ይህ ፕሮግራም መጀመሪያ በአዲስ አበባ ነፋስ ልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ አዲስ አበባ ካሉት ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች አንዱ መሆኑ ይታወቃል:: በሚቀጥሉት ደረጃዎች በሱማሌና ቤንሻንጉል ጉሙዝ በሚገኙ መጠለያ ማእከላት እንደጀምርም ተውቋል::
ከ2016 ዓ/ም እ.ኤ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ወደ ማብሀረሰቦቻቸው በማቀላለቀልና በመመለስ የታቀናጀ ከስደት ተመላሾች መርሃ ግብር ነድፋ ከአውሮጳ ህብረት ከሌሎች አለም አቀፍ አካላት ጋር በመተባበር እየሰራች መሆንዋ ይታወቃል::
TMP – 31/10/2018
Photo: NRC
ፅሑፉን ያካፍሉ