ጅቡቲ ላይ ባጋጠመ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ምክንያት የሰው ህይወት አልፈዋል
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ያወጣው መግለጫ እንደምያመለክተው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን ስደተኞች ጭነው ሲሄዱ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች በባል ኤልመንደብ መስመር በመገልበጣቸው ምክንያት የ58 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዘገበው ፌቡራሪ 1/2019 ላይ ነው።
ይህ አሰቃዊ ሁነት ያጋጠመው በሰሜናዊ ጅቡቲ ኦበክ በተባለ አከባቢ በምትገኘው ጎደርያ እየተባለች በምትጠራው ቦ ታ ላይ ነው። የአከባቢው የይን እማኞች በመጥቀስ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለጸው ጀልባዎቹ ለ30 ደቂቃ የምያህል ጊዜ ቁልቁል ሰጥመዋል። ይህ የሆነው ደግሞ ከአቅም በላይ በመጫናቸው ነው ተብለዋል።
እነዚህ ወደ አረብ ፐንዝዙላ ለመሄድ የተሳፈሩ በርከት ያሉ ስደተኞች የጫኑ ጃልባዎች ከ2014 ወዲህ ከአጋጠሙ በአሰቃቂነታቸው የሚጠቀሱ አደጋዎች ከፍተኛው ደረጃ የምይዝ አደጋ መሆኑም ተገልጸዋል።
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለጸው በኦቦክ-ጁቢቲ ከ2014 ወዲህ ይሄኛው ጨምሮ ቢያንስ ለ199 ስደተኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆኑ ሶስት ጊዜ ተመሳሳይ አደጋ አጋጥመዋል።
“ይህ አሰቃዊ አደጋ የምያሳየው ምንም የማያቁ ስደተኞች ለተሻለ ህይወት ሲሉ የሚከፍሉት ዋጋ ነው።” ብለዋል በጅቡቲ የአለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት መልእክተኛ የሆነው ላሊኒ ቬራሳሚ።
መልእክተኛው ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለጸው የ15 ዓመት ዕድሜ በህይወት ከቀሩት አንዱ የሆነው ኢድ ሞሃመድ እሱን ጨምሮ ሌሎች ወደ 80 የሚጠጉ ስደተኞች ጀልባ ተጭነው ነበር ሲሄዱ የነበሩት።
“የማስታውሰው ካፕቴኑ የጀልባው ሞተር እንደተበላሸበት እና ጀልባው እየሰመጠ መሆኑን ነው። ከዛ በኋላ የማስታውሰው ነገር የለም” ሲልም አክለዋል።
ሞሃመድ “በህይወቴ ያጋጠመኝ በጣም የከፋ ፈተና ነው። ከዚህ መዓት ያወጣኝ አምላኬ አመሰግነዋለሁ” ሲልም አክሎ ገልጸዋል።
ደሰምበር መጀመርያዎች አከባቢ “እነዚህ ስደተኞች የተሻለ ህይወት ፍለጋ፣ የቤተሰቦቻቸው ህይወት ለመቀየር፣ የተሻለ ስራ ለማግኝነት፣ ድህንነት እንዲሰማቸው እና አዳዲስ ዕድሎችን ለማግኘት ነበር ሲሄዱ የነበሩት። አብዛኛዎቹ ደግሞ ወጣቶች ስለሆኑ ያሉት ችግሮች መረዳት አይችሉም።” ብለዋል ሞሃመድ አብዲከር፡ በጅቡቲ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኦፕሬሽን እና የኢመርጀንሲ ዳይሬክተር።
“ከዚህ በተቃራኒ በመንገዳቸው ህገ ወጥ የሰው ልጅ ንግድን ጨምሮ ብዙ ጥቃቶች ይደርስባቸዋል። ወደ የመን የምያቀኑት የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ይገጥማቸዋል’ ይህ ደግሞ ወደ ሌላ ተጨማሪ ጥቃትና ችግር እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል።” በለዋል ዳይሬክተሩ።
ይህ በደቡባዊ የቀይ ባህር ጫፍ የሚገኝ እና ከአፍሪካ በኤርትራ እና ጅቡቲ ከዓረብ ፔንሱላ ደግሞ በየመን የሚዋሰን የባህር በር በኢትዮጵያና ሶማልያ ካለ ድህነት እና ግጭት ለማምለጥ ብለው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚያቋርጡት የባህር በር ነው።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ሪፖርት ከሆነ በ2018 ወደ የመን መሬት ከደረሱት 150, 000 ስደተኞች አብዛኛዎቹ በመንገድ ላይ በህገ ወጥ ደላሎች ጥቃት ደርሰባቸዋል፣ የተለያየ ጥቃት ሰለባ ይሆናሉ እንዲሁም በየመን ባሉ ደካማ የማቆያ ማእከላት ታጉረው ለሌላ ስቃይ ይጋለጣሉ።
TMP – 08/02/2019
ፎቶ ካፕሽን: በጅቡቲ እና የመን ለሚደረግ ትራንስፖርቴሽን ከሚውሉ መርከቦች አንዱ
ፎቶ ክሬዲት: ቫድምሚር መልኒክ/ሹተርስቶክ
ፅሑፉን ያካፍሉ