በ2017 ወደ ኣዉሮፓ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በ95% ቀንሷል

በ2017 ወደ ኣዉሮፓ ምድር የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር በ2016 ከነበረዉ ተመሳሳይ 12 ቀናት ዉስጥ ሲነፃፀር 95%

ቅናሽ ማሳየቱ ተገልፃል ።

እንደ IOM ዘገባ፡ ባለፈዉ አመት በመጀመርያ 12 ቀናት ዉስጥ ብቻ 22,590 ስደተኞች ወደ ኣውሮፓ የገቡ ሲሆን፡ ይህ

ቁጥር በዚሁ ዓመት ተመሳሳይ ቀናት ውስጥ ወደ 1,159 ወርዷል። በምስራቅ ሜዲትራንያን ባህር በኩል የሚጓዙት

ስደተኞች ካለፈዉ ዓመት ተመሳሳይ ግዜ ዉስጥ ታላቅ ቅናሽ ኣሳይቷል። እስከ ጥር 12 እ.ኣ.ኣ ድረስ ወደ ግሪክ ከገቡት

22,322 ስደተኞች፣ 430 ስደተኞች ብቻ ከቱርክ ናቸዉ።

በስደት የሚሞቱት ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም የሚሞቱትና በህይወት የሚገቡት ቁጥር ግን በአስር እጅ ጨምረዋል። ባለፈው

ዓመት ከአንድ ሺ ስደተኞች 3ት ሞት የሚያጋጥም የነበረዉ አሁን ከአንድ ሺህ ስደተኞች 25 ሞት ያጋጥማል። ባለፈዉ

ዓመት በተመሳሳይ ግዜ ዉስጥ ጠቅላላ 64 ሞት ያጋጠመ ሲሆን በ2017 ተመሳሳይ ወቅት 27 ሞት ተመዝግበዋል።

ምንም እኳን ቁጥሩ አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም በ2016 ከኤርትራና ከሌሎች ቦታዎች በሜዲትራንያን የገቡት ካለፉት 3

አመታት ዝቅያለ ነዉ። የምስራቅ ሜዲትራንያን በር በመዘጋቱ ምክንያት፣ የስደተኞች ቁጥር በሁለት ሦስተኛ ሲቀንስ

የሞት ቁጥር ግን በሶስት እጅ ጨምሯል ።

በ2016 ከነበሩት ስደተኞች ኣብዛኞቹ የሄዱት ከናይጄርያና ከኤርትራ ናቸዉ። በተመሳሳይ ዓመት 181,436 ስደተኞች ወደ

ጣልያነ ገብተዋል። ከነዚህ ትልቁ ድርሻ የያዘችዉ ናይጄርያ 20% ከኣፍሪካ ከተጓዙት 37,551 ሸፍናለች።

ሁለተኛዉ ትልቁ ድርሻ የያዘች ሃገር ኤርትራ ስትሆን፡ ይህም 20,718 እና ወደ 3,832 የሚጠጉ ደግሞ በተናጠል የተጓዙ

ከእድሜ በታች ሲሆኑ ይህ ቁጥር ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛዉ ነዉ ። በ2014 በትንሹ 34,329 ኤርትራዉያን

ወደ ጣልያን ገብቷል ። በ2015 በሜዲትራንያን በኩል ወደ ኣዉሮፓ ከገቡት ስደተኞች ኤርትራ በቀዳሚነት ደረጃ ተቀምጣ

40, 000 ስደተኞችዋ ወደ ጣልያን ደርስዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ 95,000 የሚጠጉ ኤርትራዉያን ስደተኞች

በጣልያን ተመዝግበዋል።

በ2016 ከሶርያ ሜዲትራንያን ለማቋረጥ ህይወታቸዉን ለአደጋ ያጋለጡት ስደተኞች ቁጥር ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፀር

97% ቅናሽ ኣሳይተዋል። በ2014 ጣልያን የገቡት 42,323 የነበረ ሲሆን በ2015 ወደ 7,448 ዝቅ ብለዋል። IOM

እንደዘገበው በ2016 ወደ 1,200 ቀንሰዋል።

በ2016 ወደ ብዙ የኣዉሮፓ አገሮች የሚገቡ የስደተኞች ቁጥር በጣም ዝቅ ብሎዋል። ከአንድ ዓመት በፊት 900,000

ስደተኞች የገቡ ሲሆን በ2016 ወደ 280,000 ወርደዋል። ይህ የሚያሳየዉ የህገወጥ የስደተኞች ቁጥጥር መጠናከሩ እና፡

በተለይ ባለፈዉ ዓመት በባልካን በኩል የተደረገዉ ቁጥጥር ዉጤታማ እንደነበረ የሚያሳይ ነው።