ስፔን ለድንበሯ የክትትል ስራ እርዳታ አገኘች
ፎቶ ክረዲት ፎሮንቲክስ የፎሮንቲክስ ሰራተኛ የቁጥጥር ስራ ሊሰራ በቁጥጥር ስራ ላይ እያለ
የሚዲቲራንያን ባህር አቋርጠው ወደ ስፔን የሚገቡ የአፍሪቃ ስደተኞች ቁጥር በ2017 ዓ/ም አሻቅቦ ነበር ፡፡ የአውሮፓ የድንበርና የባህር ዳርቻ ጥበቃ ኤጀንሲ ፎሮንቲክስ እንደሚለው በዚህ ዓመትም እንደሚጨምር ይጠበቃል ፡፡
ባለፈው አመት ወደ 22000 (ሃያ ሁለት ሺ) የሚጠጉ ስደተኞች ስፔን ገብተዋል ከ2016 ዓ/ም ከነበረው ቁጥር ሲነፃፀር 10231 መሆኑ ነው ፡፡ የፍሮንቲክስ ሃላፊ ፋብሪስ ለገሪ ማድሪድ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መስሪያ ቤታቸው ወደ ስፔን የባህር ጠረፍ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ለመቀነስ ኤጀንሲያቸው ተጨማሪ ስራና ጥረት እንደሚያዳርግ ገልፀው ይህም የስፔን የድንበር ጥበቃ ስራን በመደገፍና በመርዳት መሆኑ ገልፀዋል፡፡
“መጥፎው ዜና የምዕራባዊው ሜዲተራንያን አከባቢ ያለው ነው፡፡ ስፔን ከአውሮፓ ህብረት የጠበቀ ወዳጅነት ትጠብቃለች” ሲሉም አክለዋል ለጋሪ /ሃላፊወ/ ጨምረወ ሲናገሩ “ በጣልያንና በግሪክ ስደተኞችን ለመመዝገብ የሚጠቀሙትን የአሰራር ዘይቤ በስፔይንም ይደገማል ብለዋል፡፡
የአሰራር ዘይቤው ህግ ተርጓሚዎችን የፀጥታ አካላት የስደተኞችን የወንጀል ሪከርድ (ድርጊት) ለመለየት ከሌሎች አገሮች ኤጀንሲዎች በጋራ ለመስራት ግዛቸዋል ብለዋል፡፡
እንደ አለም አቀፍ የስደተቶች ጉዳይ ድርጅት ገለፃ ከሆነ በ2018 ዓ/ም ባለፉት ሶዎስት ሳምንታት ውስጥ ወደ 2583 ስደተኞች ባህርን አቋርጠው አውሮፓ ገብተዋል፡፡ በዚሁ ተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞች ባህሩን ሲያቋርጡ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ