የኣውሮፓ ሕብረት መሪዎች ስምምነት በመካከለኛ ሚድትራያን የሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ለመዝጋት የቀረበ እቅድ

የኣውሮፓ ሕብረት መሪዎች በሕገ-ወጥ ደላሎች መርበብ ከሊብያ ወደ ኣውሮፓ ለመድረስ የሚያደርጉት ሕገ-ወጥ ጉዞ

ለመበጣጠስ ተስማሙ።

ኣዲሱ ስምምነት በማልታስ ዋና ከተማ ቫልታ በየካቲት 3 የተደረገ ሲሆን፤ የኣውሮፓ ሕብረት ባለፈው ኣመት በቱርኪ

በተደረገው ስምምነት መሰረት ኣድርጎ ሕገ-ወጥ ስደተኞች በምስራቅ ሚድትራንያን ባህር በኩል ሊጓዙ ለሚሞክሩ

ያተኮረ ነው። ያለፉት ጉዞዎች በ6 ዓመት ውስጥ 13000 ሰዎች ህይወታቸው ኣጥተዋል።

የኣውሮፓ ሕብረት እና ቱርኪ ከተስማሙ ጀምሮ ከምዕራብ ባልኣንሳ ወደ ግሪክ የሚደረግ የስደተኞች ጉዞ ከኣለፈው

ኣመት ቀንስዋል። በ2016 ያለፉት 4 ወራቶች ከኣለፈው ኣመት ጋር ሲነፃፀር በ98 % ቀንስዋል።

ምንም እንኳን የኣውሮፓ ሕብረት በኣለም ኣቀፍ የሊብያ ወንዞች ወታደራዊ ቅኝት ያለው ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪ

ሞያ ለማሰልጠን፣ ለማቅረብ እና ለመደገፍ የሊብያ ሐገር ኣቀፍ የባህር ጠባቂዎች እና ሌሎች ወኪሎች የሕገ-ወጥ

የሰዎች ደላሎች ለማስወገድና የኣፍሪካ ስደተኞች ጥለው እንዳይሄዱ እንደተከላከሉ ሐገሪትዋ የሚያስችል ኣቅም

እንዲኖራት ማድረግ ነው።

ይህ ኣቅድ በተጨማሪ በግብፅና ቱኒዝያ ያለው የሕገ-ወጥ ዝውውር ኣማራጭ ለመዝጋትና ለማውደም ያካትታል።

በሊብያ ያሉ መጠልያ የሌላቸው ስደተኞች ለመርዳት ኣዲስ የስደተኞች ካምፕ በሊብያ ይቋቋማል።

“በምድረ በዳ እና በየባህሩ ለሚሞቱ ሰዎች ማቆም ያለው ብቸኛ ኣማራጭ ኣንድ ብቻ ነው፡ እሱም ለኣውሮፓ የሚሻገሩ

ስደተኞች መቆጣጠር ነው፡” ሲሉ የኣውሮፓ ሕብረት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ታስክ ተናግረዋል። ኣክለው ፕሬዚዳንቱ “በሊብያ

ያሉ ማሕበረሰብ ኑራቸው ለማሻሻል የኢኮኖሚ ኣቅርቦት እናደርጋለን። በተጨማሪም ለስደተኞች መጠለያ እንዲኖራቸው

እንሰራለን ብለዋል።”

ለውጥ ኣምጥተናል። በትክክለኛ መንገድ እንገኛለን። ያሉት ደግሞ የማልታስ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆሴፍ ሙሳካት ናቸው።

“ እንደሚመስለኝ የትርክ ስምምነት የሰሜን ኣፍሪካ ኣገሮች ስምምነት ልዩነት የለውም። ኣንድ ነው። ስለዚህ የሕገ-

ወጥ ስደተኞች ደላሎች በመስበር ሓቀኛና ቀጣይነት ያለው የስደተኞች ፖሊሲ እንዲኖረን ይገባል።”

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ወኪል እና የኣለም ኣቀፍ ስደተኞች ድርጅት የጥገኝነት ጥያቄ ጠይቀው

የማይመለስላቸው በሊብያ የስደተኞች ካምፕ ላሉት ጥያቄዎች በሂደት መመለስ ኣለባቸው።