በሊብያ የነበሩ የምዕራብ ኣፍሪካ ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ

TMP – 24/02/2017

አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅች 334 ስደተኞች በመሰብሰብ ወደ ትውልድ አገራቸው መልሳቸዋል፡፡በየካቲት 14 እና 16 አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በ2 በረራ 334 ስደተኞችን ከሊብያ ወደ ትውልድ አገራቸው ናይጀርያና ሴነጋል መልሰዋል፡፡

በመጀመርያ በረራ 101 ሴቶች፣ 43 ወንዶችና 18 ህጻናት ወደ ናይጀርያ ተመልሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሁለተኛ ዙር በረራ አንዲት ሴት የምትገኝባቸው 172 ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው ሴኔጋል ተመልሰዋል፡፡

በታላቅዋ ብሪጣንያ እርዳታ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞችን ወደ አገራቸው የመመለስ ፕሮግራም እየሰሩ ነው፡፡

ከነዚህ ስደተኞች ውስጥ 9 በግላቸው የተሰደዱ ሕፃናት ከቤተሰባቸው እንዲገናኙ እርዳታ ተደርጎላቸው ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በመተባበር  ወደ አገራቸው የማስገባት ስራ ተሰርተዋል፡፡ 56 ስድተኞች ደግሞ  ዳግም በመቀናጀት ወደ ኣገራቸው ሲገቡ የትምህርትና የንግድ ስራ መጀመር እንዲችሉ ተመቻችታቸዋል፡፡

አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞቹ አገራቸው ከመሄዳቸው በፊት ቃለ መጠይቅ በማድረግ የጤናቸው ሁኔታ በመረጋገጥ ልብስና ጫማ ሰጥተው ነው ወደ ኣገራቸው የሚመለሱት፡፡

አብዛኞቹ ስደተኞች እንደሚናገሩት በሊብያ ያለ የስደት ኣስከፊነት ነበር የገለፁት፡፡

ወደ አገርዋ የተመለሰችው የናይጀርያ ስደተኛ ብሪጄት አኪያሞ እንደተናገረቹ ትምህርት ከመጨረስዋ በኋላ በአገርዋ ስራ ስታጣ ቤተስብዋ ወደ ጣልያን ልሉኩዋት ወስኑ፡፡ በዚህ መሰረት ከናይጀርያ አሙና መጨረሻ ነሐሰ  ነበር የወጣች፡፡ አሁን ብሪጄት የ4 ወር ነፍሰ ጦር ሁና ነው የተመላለሰች፡፡

ብሪጄት እንደተናገረችው ከሊብያ ወደ ጣልያን ለመሄድ በሞኮረች ግዜ በስደተኘች ካምፕ መታሰርዋ ገልጣለች፡፡ “አንዴ ከተያዝኩ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት እየተዘዋወርኩ ነበር፡፡ በእስር ቤት ላይ ኢሰብኣዊ ለሆነ  ሰራ ተጋልጠናል፡፡ ከምንበላው ምግብ ጀምሮ እስከ ምንጠጣው ውሃ ቆሻሻና ለበሽታ የሚያጋልጥ ነው፡፡ ኣብዛዎቹ ወጣት ሴቶች በሊብያ በግልፅ ተደፍረዋል፡፡ ለነዚህ ትእዛዞች ለመቀበል ካልተስማሙ ከዚህ የባሰ ወደ ጋሃነመ እሳት እንደ መግባት ነው የሚጠብቃቸው፡፡ ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን እኔ ኣሁን ናይጀርያ ውስጥ ነኝ፡” ኣለች።

ሌላው ሰኔጋላዊ ስደተኛ ተመላሽ ኣብዱላይ ኒስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡ “በሊብያ የነበረው ሁኔታ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ ነበር፡፡ ለ4 ወራት ያህል እስር ቤት ነበርን፡፡ የታሰርንበት ምክንያት ኣውሮፓ ለመሄድ ስንሞኮር ባህር ላይ ስለያዙን ነው፡፡ በእስር ቤት ምግብ የለም፡፡ እንቅልፍ በአግባቡ አንተኛም፡፡ በየግዜው ስንደበደብ ነበር።”

ባለፉት 10 ዓመታት ወደ አገራቸው የመመለስ ፍላጎት ያለቸው ስድተኞች ማለትም የመኖርያ ፍቃድ ለማግኘት ያልተሳካላቸው 412,000 ስደተኞች አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት  ወደ አገራቸው ለመመለስ ኣማቻችተዋል፡፡ ከተመለሱት መካከል ታግተው የነበሩ የሕገ ወጥ ዝውውር ተጠቂ ስድተኞች፡ የጤና ችግር የነበረባቸውና ብቻቸውን የነበሩ ህፃናትና ይገኙባቸዋል፡፡