ፈረንሳይ በአልፕስ ግዛት በፀረ ስደተኛ ሀይሎች እና ስደተኞች መሀከል የተከሰተውን አለማግባባት ለማርገብ ፖሊስ ላከች
የፈረንሳይ መንግስት ፈረንሳይን ከጣልያን ጋር በምታገናኘው አልፕስ ግዛት አከባቢ ህገ ወጥ ስደትን በሚቋወሙ ሀይሎችዋ እና ስደተኞች ያጋጠመውን አለማግባባት ለማርገብ የፖሊስ ሀይል መላክዋን ተገለፀ።
በግንቦት ወር የወሩ ሶስተኛው ሳምንት ላይ የፈረንሳይ ፓርላማ ከፍተኛ ክርክር በማድረግ ያፀደቀውን አዲስ የስደተኞች አያያዝ ህግ ተከትሎ በርከት ያሉ ፈረንሳውያን ያገባኛል ባይ ዜጎች (activists) የህጉ መፅደቅ ደግፈዋል። ከመደገፍም አልፈው ፈረንሳይን ከጣልያን ጋር በምታገናኝ የአልፕስ ግዛት ባሉ ስደተኞች የሚገቡባቸው ተራሮች ላይ ኬላ ሰርተው ስደተኞችን ማገዳቸው ይታወሳል።
እነዚህ ያገባኛል ባይ (activists) ፀረ ህገ ወጥ ስደተኞች የሚንቀሳቀሱ የፈረንሳይ ቡድኖች ግንቦት 21 ላይ ከቦታው ተገኝተው ቦታው “strategic point for illegal migrants” ማለትም “ህገ ወጥ ስደተኞች የሚያልፉበት ቁልፍ ቦታ” በማለት ገለፀውታል።
በእርግጥም ህገ ወጥ ስደተኞች ከጣልያን ተነስተው ፈረንሳይ ለመግባት የሚጠቀሙበት በር ነው፤ አልፕስ።
ይህ ክስተት ሌላ ተቃርኖ ቀስቅሰዋል። የስደተኞቹ ሁኔታ ያሳዘናቸው አካላት ከስደተኞች ጎን ( pro-migrant) የቆሙ ቡድኖች የአውሮፓ ሀገራት በራቸው ይከፍቱ ዘንድ ይሞጉታሉ። በዚህ እንካስላንትያ ምክንያት ከፈረንሳይ እና ጣልያን የተተውጣጣ የፀረ ስደተኞች ቡዱኑ እና 30 የሚሆኑ ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ ሞንተገነቭሪ በሚወስድ መንገድ ፊት ለፊት ተገናኝተው ጠቡ ወደአልተፈለገ መንገድ ሊሄድ ችለዋል። ከፀጥታ ሀይሎችም ለመጋጨት ችለዋል።
ግጭቱን አስመልክተው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዳሉት “ወንጀሉ በፀጥታ ሀይል ላይ የተፈፀመ ወንጀል መሆኑ መታወቅ አለበት። የአደጋ መከላከያ መሳርያም (gendarme ) ተጎድተዋል” ብለዋል።
የፈረንሳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ጨምረው እንዳሉት ከድንብር ቁጥጥር ስራው ተያይዞ የተደረገ አለመግባባት እና ግጭት አለስፈላጊ እና ተቀባይነት የሌለው ነው። እሳቸው እንደገለፁት የፀጥታ ሃይሎች የሀገሪቱን ህጎች ተፈፃሚ ያደርጉ ዘንድ ተልእኮ የተሰጣቸው በመሆናቸው የስደተኞቹ ድርጊት አስነዋሪ ተግባር ነው ብለውታል። እናም “በፀጥታ ሀይሎቻችን እና መሳርያቻቸው ላይ የሚደርስ ማነኛውም ጥቃት ተቀባይነት የሌለው ትንኮሳና ግጭት ተቋቁመን ህገ ወጥ ስድተኞችን የሚቆጣጠር ጠንካራ ግብረ ሀይል አደራጅተናል።” ብለዋል ሚኒስትር ኮሎምብ።
ሚኒስትሩ ጨምረው እንዳሉት አዲስ የተላኩ የፀጥታ ሀይሎች በአከባቢው ያለ የፀጥታ ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የምያስችል ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ የፈረንሳይ ሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ብሪስ ሆርተፊክስ ከፈረንሳይ ሚደያ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የስደተኞቹ ጉዳይ በዚህ ደረጃ ሊታይ እንደማይገባ እና የአንዳንድ ጫፍ የሄደ አመለካከት ያላቸው ያገባኛል ባዮች (activists) የተመቸ ነው። እሳቸው “ይህ ተነሳሽነት (initiative) ሙሉ በሙሉ እቃወመዋለሁ። ነገር ግን ያገባኛል ባዮቹ የያዙት አቋም እያስተላለፈው ያለ መልእክትም በትክክል መረዳት ያስፈጋል” ብለዋል።
ግንቦት 22 ላይ የፈረንሳይ ፓርላማ የስደተኞችን ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ የምያስገባ አዲስ ህግ ማፅደቁ ይታወሳል።
አዲሱ የስደተኞች መቆጣጠርያ ህግ፤ ህገ ወጥ ስደተኞችን በተሻለ መልኩ ለማስተናገድ ታስቦ እንደወጣ ይነገራል። ከያዛቸው ነጥቦችም የመጥግያ ጥያቄ ያላቸው ስደተኞች የመስጠት ሂደቱ ፈጣን እንዲሆን፣ መመለስ ያላባቸው ተሎ እንዲመለሱ ለማድረግ እና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ፈረንሳይ ለሚገቡ ደግሞ የአንድ ዐመት እስር እንዲፈረድባቸው የሚሉ ይገኙበታል።
የዚህ ምክንያትም የቁጠባ ስደተኞች (economic migrants) ተብለው የተፈረጁ በተለይ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞች ስለሚገኙባቸው መሆኑም ተገልፀዋል።
TMP – 10/06/2018
ፅሑፉን ያካፍሉ