በግሪክ በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ውስጥ የከፋ ፆታዊ ጥቃት በስደተኞች ላይ እንደሚደርስ ታወቀ
ፎቶ ክረዲት፡- ጌቲ ሞይራ የስደተኞች ማቆያ ማእከል
እንደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ገለፃ ከሆነ በግሪክ በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ውስጥ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ አሰቃቂ ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ እንደሚደርሰባቸውና በሃገሪቱ ውስጥ ከሚገኙና በዙ ስደተኞች በሚኖሩባቸው ማእከላት የባሰ እንደሆነ ይገለፃል፡፡
“በግሪክ ደሴቶች ውስጥ ባሉት ካምፖች በሚኖሩ በመቶዋች የሚቆጠሩ ስደተኞች ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ እንደሚደርስባቸው” የኤጀንሲው ቃል አቀባይ የሆኑት ቸቺሌፑሊ በአፅንኦት የገለፁ ሲሆን ይህንንም ጥቃት በተለያዩ የፍራቻ፣ሃፍረትና ፣መገለል የበቀል እርምጃና መድልዎን በመፍራት እንደማይገልፁ ተናግረዋል፡፡”
“ የፆታዊ ጥቃቱና ትንኮሳው ከሚዘገበው በላይ እንደሚሆን ፑሊ በጀኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህንን ሁኔታ በሚመለከት በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ በሚመለከት በጣም ያመሰ ገፅታ እንደሚያውቅ ገልፀዋል፡፡11 ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባት ሃገር ባለፈው ዓመት 58661 ስደተኞች ተገን ጠያቂዎች አስተናግዳለች፡፡ ይህም ግሪክ ከአውሮፓ ሃገሮች ተቀዳሚ የስደተኞች አስተናጋጅ መሆንዋ ያሳያል ሲል የግሪክ የተገን ጥያቄ አገልግሎት ክፍል ይገልፃል፡፡
ፑሊ ጨምረው እንዳስረዱት” በስደተኞች ካምፖች በተለይም በሞይራ፣ ሌስቦስ፣ቫቲ ኦንሳምስ በመሳሰሉት መጠልያዎች በኚዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ለድህንነታቸው አስጊ በሆኑ ሁኔታ ላይ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡”
በዚህ አስከፊ ሁኔታ ደግሞ ተጠቂዎቹ ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውና ይህም በብዛት ስደተኞች በሚኖሩባቸው ማእከላት ባለው የሰው ብዛት እንደሆነ ወደ 5500 ህዝቦች መሆናቸውና ይህም ከአቅማቸው በላይ በእጥፍ እንደጨመረ ታውቋል፡፡
“ ዚህ ሁለት ማእከላት የሽንት ቤቶች ባኞ ቤቶች በጨለማ ወቅት የማይኬድባቸው ስፍራዎች መሆናቸው ፑሊ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በቀን ገላን መታጠብ ራሱ አስጊ እየሆነ መሆኑ ተናግረዋል፡፡”
lበሞይራ ማቆያ ማእከል ያለች አንዲት ሴት ለሁለት ወራት ገላዋን እንዳልታጠበችና ይህም ፆታዊ ጥቃት እንዳይደርስባት በመፍራት መሆኑ ገልፃለች፡፡
በተመሳሳይ ማቆያ ማእከል ሃላፊዋ ሲገልፁ 30 የሚሆኑ የመንግስት ሰራተኞች፣ የስነ ልቦና ኣማካሪዎች፣የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኞች በአንድ ላይ በ3 ጠባብ ክፍሎች ታጭቀው የህክምና ምርመራ ፣የተለያዩ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡
በአቴንስ /ግሪክ መንግስት/ የሚወሰዱ ጾታዊ ጥቃትን የሚቀንሱ እርምጃዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚደገፉና ሴቶች ወንዶች የሚኖሩባቸው ክፍሎች መቀራረብ እንደሌለባቸውና ከሚያውቋቸው ወንዶች አጠገብ ሴቶች መቀመጥ እንደሌለባቸው ደጋግመውና እጥብቀው ይመክራሉ፡፡
የተባበሩትመንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲው የስደተኞች ቁጥር ኣናሳ እንዲሆን በመፃዳጃ ቤቶችና ሻወሮች በቂ መብራት እንዲደረግባቸውና የድህንነትና ፖሊሶች ቁጥርም መጨመር እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ግሪክ ባለፈው ወር ስድተኞች ከመቀበል አንፃር ከአቅምዋ በላይ እንደተቀበለች ትልቁ ጫና እንደደረሰባት ስትገልፅ የተገን ጥያቄዎች በ2017 ከቀረበው ማመልከቻ 8.5% ከአውሮፓ ህብረት ከቀረበው ጥያቄ ማስተናገዷ አስታወቃለች፡፡
11 ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባት ሃገር ባለፈው ዓመት 58661 ስደተኞች ተገን ጠያቂዎች አስተናግዳለች፡፡ ይህም ግሪክ ከአውሮፓ ሃገሮች ተቀዳሚ የስደተኞች አስተናጋጅ መሆንዋ ያሳያል ሲል የግሪክ የተገን ጥያቄ አገልግሎት ክፍል ይገልፃል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ