ጀርመን ወደ አገራቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመመለስ ለመረጡት ስደተኞች የሚሰጥ ጥቅም ላይ ጭማሪ አደረገች
ጀርመናውያን በሰልፍ ላይ እንዳሉ ፡፡ ፎቶ፡ ሾን ጋሉፕ/ ጌቲ ኢሜጅስ
የጀርመን መንግሥት ጥገኝነት ጠይቀው ላልተፈቀደላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አገራቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመመለስ ከመረጡ፣ እስከ ሦስት ሺ ዩሮ በመስጠት ላይ ነው፡፡
የፌደራሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር “ያንተ አገር፣ ያንተ የወደፊት ዕጣ፣ አሁን” የተሰኘ አዲሱ ፕሮግራም እስከ የካቲት መጨረሻ 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ አስታወቀ፡፡ በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዌብ ሳይት መሠረት ፕሮግራሙ የሚያጠቃልለው “ክፍያዎች፣ አንዳንድ ጥቅሞች በዓይነት ለምሳሌ ለቤት ኪራይ ድጋፍ መስጠት፣ ለግንባታ ወይም ለእድሳት ወይም ለማድ ቤትና ወይም ለገላ መታጠቢያ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮችን” የመሳሰሉትን ነው::
ባለፈው የካቲት የተጀመረው አዲሱ “ጃምፕ ስታርት ፕላስ” የተሰኘው ፕሮግራምን ያሟላል፡፡ በአዲሱ አሠራር መሠረት ቤተሰቦች እስከ ሦስት ሺ ዩሮ (3570 ዩ.ኤስ ዶላር)፣ ለግለሰቦች ደግሞ እስከ አንድ ሺ ዩሮ (1190 ዩ.ኤስ ዶላር) በ“ጃምፕ ስታርት ፕላስ” ከሚደረገው ክፍያ በተጨማሪ ይገባቸዋል፡፡
የፌደራሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቶማስ ደ ማይዚየረ ከብሔራዊ ጋዜጣ ከቢለድ አም ዞንታግ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በእቅዱ መሠረት ወደ አገር መመለስ የሚያስገኘው ጥቅም ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ደ ማይዚየረ ንግግራቸው ሲቀጥሉ “በአገራቹህ ሥራ ለመሥራት ምቹ ጊዜ ይኖራቹኋል፣ እዛው ለመወሃሃድ እንድትችሉ እኛ እንረዳችኋለን” ብለው ተናገሩ፡፡ በየካቲት ወር መጨረሻ በበጎ ፈቃደኝነት ለመመለስ ከወሰናችሁ፣ በተወለዳችሁበት አገር ከየመጀመርያ እርዳታ በተጨማሪ፣ ለመጀመርያ 12 ወሮች የቤት እርዳታ ታገኛላችሁ አሉ፡፡
እስከ አሁን ድረስ በጀርመን አገር ጥገኝነት ጠያቂዎች የጥገኝነት ማልከቻቸው ውሳኔ ከማግኘቱ በፊት በበጎ ፈቃደኝነት ወደ አገራቸው ለመመለስ ከጠየቁ € 1200 ዩሮ ሲሰጣቸው ቆይቷል፡፡ ማመልከቻቸው ተቀባይነት ካላገኘ €800 ዩሮ ይሰጣቸዋል፡፡
ይህ ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የመገፋፋት ነገር የመጣው ጀርመን በአገርዋ ስደተኞችን በሚመለከት ያወጣችው “በርን ክፍት” “open door” የማድረግ ፖሊሲ መሠረት በማድረግ ነው፡፡
ባለፈው ዓመት ሦስት መቶ ሺ የሚሆኑ ጥገኝነት አመልካቾች ማመልካቻቸውን በጀርመን መንግሥት ተቀባይነት አላገኙም፣ በዚሁ ምክንያትም ስደተኞችን ከአገር የማስወጣት ሥራ በከፍተኛ አድጓል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ