ከ80 በላይ ስደተኞች ከሊብያ ወደ መጡበት አገር እንደሚባረሩ ታወቀ

ፎቶ፡ የፈረንሳይ ዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፡ የአፍሪቃ ስደተኞች በሊብያ እስር ሳሉ የሚሳይ

ከኤርትራ፣ከኢትዮጵያና ከሱማሌ ፈልሰው በሊብያ እስር ቤት ታጉረው የነበሩና ከሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ያመለጡ ወደ 81 የሚጠጉ ስደተኞች ከሊብያ ወደ መጡባቸው አገራት እንደሚላኩ የምስራቃዊው ሊብያ አስተዳደር ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ስለ ስድተኞቹ የተናገሩት አንድ የደቡባዊ ሊብያ መስጅድ ኢማም መሆናቸው ታውቋል፡፡ እንደ ኢማሙ ገለፃ “ ዛይቲና በተባለው የስደተኞች ማቆያ ማእከል የነበሩት ሕገ ወጥ ስደተኞች መታሰራቸውና አሕመድ አልኣሪፊ የተባሉ በቤንጋዚ ከተማ ግዛት የፀረ ሕገ ወጥ ስደተኞች ሰራተኛ ሲሆኑ የታሰሩት በሙሉ ወደ የመጡባቸው ሀገራት እንደሚባረሩ አስታውቀዋል፡፡”

ሊብያ ወደ አውሮፓ ለመሸጋገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ዋና መተላለፍያና መነሃርያ መሆኑዋ በታወቅም ካለፈው አመት ጀምሮ የስደተኞች ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ መመጣቱ ይታወቃል፡፡ይህም የሆነበት ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎች ስደተኞችን ስለሚያግዱዋቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
አሪፈ እንደሚሉት ከሆነ 5686 ስደተቶች ከምስራቃዊው ሊብያ ወደ ሃገራቸው እንደተባረሩና ከአምናው 2016 ወደ ነበረበት 2912 መጨመሩ ታውቋል፡፡

አንድ ከኤርትራ የመጣ ስደተኛ እንደገለፀው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ከሱዳን ወደ ሊብያ እንደገባና ለጉዞም 4,000 /ኣራት ሺ/ የአሜሪካ ዶላር እንደከፈለ ገልፀዋል፡፡ ይህ ስደተኛ በሰሃራ በረሃ በኩል ወደ ምዕራባዊው የሊብያ ግዛትና የሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ዋና መተላለፍያ መንገድ የሆነው ሳብራታ በተባለው አከባቢ ከሌሎች ስደተኞች ጋር ለ4 ወራት ያህል እንደጠበቀና በባህር የሚደረገው ጉዞ እንደተዘጋ መስማቱ ይናገራል፡፡ እንደ ሮይተርስ ዘገባ፡፡

ታጣቂ ቡዱኖች በሳብራቷ በሓምሌ ወር ስደተኞችን በጃልባዎች የሚያደርጉት ጉዞ የሚከለኩሉት ሲሆኑ በመስከረም ወር ደግሞ ከከተማዋ ተጠራርገው እንዲወጡ መደረጉ ታውቋል፡፡ኤርትራዊው ስደተኛ እንደሚለው ከሆነ ከባኒ ዋሊድ ከተማ አጅዳብያ የተባለች የሊብያ ምስራቃዊት ከተማና ለዘይቲና ቅርብ መሆኑዋ ይታወቃል፡፡ ህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ አውሮፓ ለማሸጋገር ሌላ ተጨማሪ 2,000 የአሜሪካ ዶላር እንደሚጠየቁ ገልፆ፤ ይህን የገንዘብ መጠን መክፈል ባለመቻሉ ከስቃይ ኑሮና ከእጃቸው አምልጦ መምጣቱ ይናገራል፡፡
“ ወደ ጣልያን አገር ለመሄድ ሓሳብ ነበረኝ ሆኖም አልተሳካም ሲልም ይገልፃል፡፡ በአገራችን በድህነትና በአምባገነናዊ አገዛዝ ተማረናል” ሲልም ብሶቱ ይናገራል፡፡ “አሁን ደግሞ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ስንሰቃይ ቆይተን በበሽታና በቆዳ በሽታ እንሳቃያለን ይላል፡፡ ወደ አገራችን ኤርትራ መመለስ አንፈልግን፤ወደ አውሮፓ መሄድ ነው የምንፈልገው” ሲልም አክሎ ይገልፃል፡፡