በኣፍሪካ የተሻለ ለስደት የሚመለከት ህግ እንዲኖር ጥሪ ቀረበ
አቶ አሮን ተክለዝጊ የተባሉ የድርጅቱ ባለስልጣን አፍሪካውያን ስደተኞች ከአሁጉሪቱ ሳይወጡ እንዴት መስራት እንሚፈልጉ ሲያብራሩ “አፍሪካውያን ስደተኞች በአህጉራቸው ውስጥ በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ሳትፈቅድ አውሮፓ አፍሪካውያን ስደተኞችን እንድትቀበል መጠበቅ ስህተት ነው” ብለዋል፡፡
አቶ አሮን የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት (HESPI) አዲስ አበባ ውስጥ በመጋቢት 10-2017 በክፍለ አህጉሩ የስደት ክልከላ እያስከተለ ያለው እንደምታ አስመልክተው ባቀረቡት ጽሁፍ ነው፡፡
“ለስደተኞች ብዙ ወጪ የማይጠይቅ ህጋዊ መንገድ ካልዘረጋን ሰዎች በጣም አደገኛ መሆኑ አያወቁም ህገወጥ መንገድ በመምረጣቸው ይቀጥላሉ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አቶ አሮን መልእክታቸው ወደ ስምንቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (IGAD) አባል ሃገራት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ ያነጣጠረ መሆኑም ተገልጿል። እነዚህ አገሮች የውጫዊና ውስጣዊ ስደት ዋነኛ ምንጭ መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ አገሮች 8 ሚሊዩን ስደተኞችን የሚወክሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 5.6 ሚሊዩን ከቀያቸው የተፈናቀሉ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ በሌሎች የአፍሪካ መካከለኛና የባህር ስላጤ፣ አዉሮፓና ሰሜን አሜሪካ አገራት በስደት በእንደሚገኙ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) መረጃ ያስረዳል።
በፎረሙ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት (HESPI) ማኔጂንግ ዳሬክተር የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ ስራ አጥነትና፣ የስራ ገቢ ዝቅተኝነት በተለይ በኢጋድ ክፍል አህጉር ለሚገኙ ወጣቶች ለስደት የሚያስገድድዋቸው ምክንያቶች መሆናቸው ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አፍሪካውያን ስደተኞች በአህጉሪቱ በነጻ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ የሚያጋጥማቸው ችግር መፍታት የሚያስችል ፕሮግራም ለመቅረጽ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
የኮሚሽኑ የስደት ጉዳይ አማካሪ ፒተር ሙዱንግዌ አፍሪካውያን በአህጉራቱ በነጻነት ለመንቀሳቀስና ለመስራት የሚስችላቸዉ የ10 ዓመት ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለፎረሙ አረጋግጠዋል።
ይህ በ2018 መጀመሪያ ላይ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ፅሑፉን ያካፍሉ