ጣልያንና ሊቢያ ህገ-ወጥ የስደተኞች ዝውውር ለማቆም በህብረት እንደሚሰሩተስማሙ
ፎቶ ክሬዲት፡ ኤ.ቢ.ኤል -ሲቢኤን ኒውስ የአፍሪቃ ስደተኞች ወደ ባህር ዳርቻ በእግር ሲጓዙ በትሪፐሊ በነፍስ አድን ሰራተኞች ከሜዲተራንያን ባህር ከወጡ በሃላ በሊብያ የባህር ጠረፍ
ወደ አውሮፓ ህብረት የሚደረገው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ህገ-ወጥ አዛዋዋሪዎችን ለማቆም ጣልያንና ሊብያ የጋራ ኦፕሬሽን /ግበረ ሃይል/ ለማቆም መስማማታቸው ተገለፀ፡፡
ይህ ኣዲሱ የጋራ የውል ስምምነት የተገለፀው ታሕሳስ 9 2017 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው ማእከላዊ በሊብያ መንግስት ሃላፊና ፈይዝ ስራጅ የሊብያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ኣሪፍ ከድጃ የጣልያን አቻቸው ማርኮሚኒቲ መካከል በትሪፖሊ የተደረገው ውይይት መሰረት ነው፡፡
የጋራ ግበረ ሃይል ማእከሉ የሚያአትተው የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች የህገ- ወጥ ስደት ጉዳይ የሚከታተለው ዲፓርትመንት /መምርያ/ እና የጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲሁም የሁለቱም ሃገሮች የድህንነት አገልግሎት አካላት እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ማእከሉ የት ቦታ እንደሚቋቋምና እንዴት እንደሚሰራ የተባለ ነገር/የተገለፀ ነገር/ የለም፡፡
በስደተኞች ጉዳይ ብዙ የተሰሩ ነገሮችና የተሳኩ ቢኖርም ከመጠልያ ውጭ የሚኖሩ ስደተኞች ቁጥር አሁንም እንደሻቀበ ነው፡፡ ብዙ ትብብር እንፈልጋለን፡፡ በተለይም የደቡብ ሊብያ ጠረፍና ስድተኞች በብዛት የሚጎርፍበት አከባቢ ሲሉ ፌይዝ ሲራጅ የሊብያ መንግስት ሃላፊ ተናግረዋል፡፡
ሊብያ ወደ አውሮፓ በባህር ለመጓጓዝ የሚሞኮሩ ህገ-ወጥ ስደተኞች ዋና መሸጋገርያና መናሃርያ መሆኑዋ ይታወቃል፡፡ከሃምሌ ጀምሮ የስደተኞች ቁጥር በእጅግ የቀነሰ ቢሆንም በጣልያን ተፅእኖ ምክንያት የሊብያ ተቀናቃኝ ሃይሎች ባለስልጣናት ከሊብያ የሚደረገው ህገ-ወጥ ጉዞ እየገቱና እያቆሙ መሆኑ ታውቋል፡፡
የጣልያን መንግስትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር በሜዲተራንያን ባህር ለሚደረገውህገ- ወጥ የባህር ጉዞ ለማስቆም ጥረቷ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በትሪፖሊ የባህር ወደብ ህልውናን በማጠናከር ለሊብያየጠረፍ ጠባቂዎች የፋይናንስ፣የቴክኒክና አቅርቦት /ሎጂስቲክስ/ ድጋፍ እንደምታደርግም ታውቋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ