በሊብያ ባህር ዳርቻ ስድተኞች በመታፈን ሞቱ

TMP – 12/03/2017

በምዕራባዊ የሊብያ ጠረፍ ከተማ አከባቢ በኮንቴይነር ውስጥ በመታፈን ምክንያት የሞቱት የ 13 ሰዎች ሬሳ መገኘቱ በሊብያ የቀይ ጨረቃ የካቲት 23 ኣስታወቀ፡፡ ከሞቱት ሰዎች መካከል ሁለቱ የአስራው ጉራ ህፃናት መሆናቸው ታውቋል፡፡ እንደ ቀይ ጨረቃ ሪፖርት ከሆነ 56 የሚሆኑ ስደተኞች ከሞት የተረፉት በተለያዩ ጉዳቶች እየተሰቃዩ መሆናቸውና የአካል መጉዳት የአጥንት ውልቃት የደረሰባቸውና አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል፡፡

ስደተኞች የተገኙት የካቲት 21 በጠረፍ ከተማ በሆነችውና በምስራቃዊ የሊብያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ አጠገብ ነው፡፡ እንደ  ባለስልጣናት ገለፃ ከሆነ ስደተኞቹ ለ 4 ቀናት ያህል በብረት ኮንቴይነር ውስጥ ታሽገው መቆየታቸው ታውቋል፡፡ የመጓጓዣ ኮንቴይነሩ ከማእከላዊ ከተማ ባኒዋሊድ ወደ ጠረፍ ከተማ የሆነችው ኮምስ ይጓጓዝ ነበር፡፡ ሕገ-ወጥ የሰው አዛዋዋሪዎች ስደተኞቹን ወደ ሚዲተራንያን ባህር ጀልባ ለመላክ እቅድ እንደነበራቸውና ወደ ባህር ዳርቻው ከመድረሳቸው በፊት ሕገ-ወጥ የሰው አዛዋዋሪዎች ስደተኞቹን ወደ አንድ የስደተኞች ማቆያ ማእከል የሆነው ኮምሳ ውስጥ ኣራግፋቸዋል፡፡ የበጎ ፍቃድ ሰራተኞች በደረሱ ጊዘ የመጀመርያ ህክምና እርዳታ የስነ ልቦና ምክር፣ ምግብና ብርድ ልብስ ለ 56 ከሞት የተረፉት ተጓዦች ከነሱ መሃል ስሟ አይሻ የምትባል የ 5 አመት ህፃን ትገኛለች ሲል የቀይ ጨረቃ ቃል አቀባይ ገልፀዋል፡፡

በሊብያ የባህር ጠረፍ የስደተኞች ሞት ቀጥሏል፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ 300 በላይ ደርሷል፡፡ ባለፈው ወር የ 74 ሰዎች አስከሬን በምዕራባዊው የዳርቻ ከተማ ዛውያ መገኘቱና ከትሪፖሊ በስተምዕራብ በባህር ላይ ሞተር አልባ ጀልባ ተንሳፎ መገኘቱ ይታወቃል፡፡