ሕገ-ወጥ ደላሎች 37 አፍሪካውያን ስድተኞች ገደሉ

TMP – 26/03/2017

በመጋቢት ወር በመጀመርያው ሳምንት አመፀኞች ሰዎች በሊብያ 37 ኣፍሪካውያን ስድተኞች ገደሉ፡፡ በሌላው አጋጣሚ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እንደአለው ከተገደሉ 37 ስድተኞች 22ቱ ከአመፀኞች ሲታገሉ ነው፡፡ ሲል የአለም አቀፍ ስድተኞች ድርጅት ቃል ኣቀባይ በ መጋቢት 7 ገለጡ፡፡ ቃለ ኣቀባዩ እንደጨመሩት መረጃ ከሆነ ሌሎች 100 በትግሉ ግዜ ቆስለው ነበር፡፡

በሌላው ኣጋጠሚ ዓመፀኞችን በምዕራብ ሊብያ ከተማ ሳብራታ 15 ኣፍሪካውያን ስደተኞች ገድለዋል ሲል  ዘ ሊብያ ኦብዘርቨር ገለጠ፡፡ የስድተኞቹ ሬሳ ካቆሰላቸው ጥይት ጋር በ ፋናር በረሃ አከባቢ ባህር ዳርቻ ተገኝተዋል፡፡

ይህ ግድያ በግልፅ የተጀመረው ለሕገ-ወጥ ስድተኞችን መንገድ የሚመሩ ደላሎች ከመጠን በላይ የሆነ ክፍያ በመጠየቃቸው ምክንያት በተፈጠረ ትግል ነው፡፡

በዘገባው መሰረት ደላሎች ለ 175 አፍሪካውያን ስድተኞች እያስከፈሉ ባሉበት ግዘ ነው ይህ ግርግር የተፈጠረው፡፡ በሌላው ሓሳብ ደግሞ 160 ስደተኞች እስከ አሁን የት እንደገቡ ኣይታወቅም፡፡

በቅርብ ግዘ የመጣ ዜና 140 አስኬሬን ስድተኞች ከ ሊብያ ባህር ዳርቻ ተገኝተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተገኘው አስከሬን በጣም የቆዩ ናቸው፡፡ እንዲሁም 422 ወደ ኣውሮፓ ለመሻገር በሊብያ ለመግባት ሲሞክሩ የሞቱ ናቸው፡፡

አለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት እንዳለው የፖለቲካ ቀውስ የሚሰጠው የሃይል ክፍተት ባለፉት 6 አመታት የሕገ-ወጥ ኣሸጋጋሪዎች ትርፍ ለማግኘት የተለያዩ ዓይነት ጭቆና ሊፈጽሙ ፈቅዶላቸዋል፡፡