በ 2017 ከ500 በላይ ስድተኞች በባህር ውስጥ ሞተዋል
TMP – 31/03/2017
የዚህ ዓመት የመጀመርያው 10 ሳምንታት በሜድትራንያን ባህር የጠለቁ ስድተኞች ጨምረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የባለፈው አመት ከዚህ ወቅት ሲወዳደር በጣም እየጨመረ መሆኑን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታውቀዋል፡፡
በአለም አቀፍ የስድተኞች ድርጅት በኩል በሚደረገው በባህር ውስጥ የሞቱ ስድተኞች ፍለጋ በመጀመርያው አመት እስከ መጋቢት 14 ድረስ 525 ሬሳ እንደደረሰ አስታውቀዋል፡፡
ይህ ሪፖርት እንደሚያስረዳው 14 መጋቢት 19,563 ስደተኞች ጉዞ ለመጀመር ወደ አውሮፓ በባህር የገቡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ወደ ባህር የገቡ ስደተኞች ከ 80% በጣልያን በኩል፡ የተቀሩት ደግሞ በስፔንና ግሪክ በኩልየገቡ ናቸው። የስድተኞች ፍሰት ከባለፈው አመት ከነበረው ሲነፃፀር ያነሰ ቢሆንም፤ በተመሳሳይ በ 2016 የሞቱ ስደተኞች ቁጥር በመጨመር በድምር 482 እንደጠፉ ሪፖርቱን ኣስታውቀዋል።
በሌላው በኩል ደግሞ በርካታ ስደተኞች አደገኛው መንገድ በማቋረጥ በሊብያ ወደ ኢታሊ የስድተኞች ጉዞ በእጥፍ እንደጨመረ ተገልጠዋል፡፡ ከሊብያ ወደ ጣልያን በድምር 13,439 ስደተኞች በመግባት፡ ከባለፈው አመት የነበረ የስድተኞች ብዛት በእጥፍ ጨምሮዋል፡፡
በሊብያ የሚገኘው አለም ኣቀፍ የስድተኞች ድርጅት እንደገለጠው በሊብያ ባህር ዳርቻ በአማፅያን ቀጣይነት ያለው አደጋ በስደተኞች ላይ እንደሚያጋጥም ገልጠዋል፡፡
እስከ መጋቢት 11 በሳብራታ በጠቅላላ 148 የሚያህሉ ሬሳዎች ተሰብስበዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ