ለ19 ቀናት ባህር ላይ የቆዩ ስደተኞች ወደ ወደብ በሰላም መውጣታቸው ተሰማ

49 ስደተኞች ለ19 ቀናት ሙሉ ባህር ላይ ቆይተው በስተመጨረሻ በሁለት የጀርመን ህይወት አድን መርከቦች ጃንዋሪ 9/2019 በሰላም በማልታ ወደብ ላይ እንድያርፉ ተደርጓል። እነዚህ ከዘጠኝ የአፍሪካ ሃገራት የመጡት ስደተኞች አራት ሴቶች እና ስድስት ልጆች የሚገኙባቸው ሲሆኑ ወደ አውሮፓ መውጣት እንዳይወጡ ተከልክለው የነበሩ ናቸው። አሁን ግን ወደ ዘጠኝ የአውሮፓ ሃገራት እንዲሄዱ ይደረጋል።  

49ኙ ስደተኞች በህገ ወጥ  መንገድ በሊብያ በኩል ወጥተው ሜዲትራንያን ባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመድረስ ነበር የተነሱት። በመንገድ ላይ እያሉ ነበር በጀርመኑ በሩቅ እይታ መነፅር አማካኝነት  የህይወት አድን መርከብ ባደረገላቸው እገዛ ነው የወጡት።

የባህሩ የአየር ሁኔታ ብዙ ስደተኞች ወዳልተፈለገ የባህር በሽታዎች የዳረጋቸው ሲሆን የህይወት አድን መርከበኞቹ እንደገለፁት ደግሞ ህይወታቸው ይድን ዘንድ ስደተኞቹ ያቀረቡት ጥሪ ሁሉንም የሜዲትራንያን ባህር አዋሳኝ ሃገራት ጀሮ ደባ ለበስ ብለው መቆየታየቸው ተናግረዋል። እንደ ዘኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ከሆነ የጣልያን መንግስት ድጋፍ ለመስጠት አስቦ የነበረ ቢሆንም ድጋፉ ከሊብያ መንግስት  ጋር የምያገናኝ ነገር ስላለው ሀሳቡ ለሊብያ ቀርቦላት ሳትቀበለው ቀርታለች።

ከሶስት ሳምንታት በኋላ ነው እንግዲህ እነዚህ ባህር ላይ በአደጋ ውስጥ የነበሩ ስደተች በጃንዋሪ 1/2019 ማልታ እሽታዋን ገልፃ ተቀብላቸዋለች። የማልታው ጠቅላይ ሚኒስትር  ጆሴፍ ሙስካት ትኩረት ሰጥተው እንደተናገሩት ስደተኞቹ የማውጣት ውሳኔ የተለየ ውሳኔ ነው ብለዋል። አክለውም “እንደባለፈው ነው ይሄንንም ያደረግነው። ጉዳዬ የተለየ እና አሁን ብቻ የተደረገ አይደለም” ብለዋል።

የጣልያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሉጉይ ዲ ማዮ በበኩላቸው ማልታ የሰደተኞች መርከብ በወደባ ላይ እንድያርፉ ከፈቀደች ጣልያን የተወሱ ስደተኞችን ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነች ገልፀዋል። ይሁንና የቀኝ ዘመም ፓርቲ ሊቀመንበር እና የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ማቲው ሳሊቪኒ በነበረው አቋማቸው ፀንተዋል። በመሆኑም “መንግስታችን መንግስት ሆኖ ከተመረጠበት ጊዜ ጀምሮ በስደተኞች ላይ ያለው አቋም  እንዲጠነክር ሰርተዋል።  ስደተኞች የምያርፉባቸው ወደቦችን በተለያዩ ግዝያት ዘግተዋል። “ ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአጠቃላይ ወደ አውሮፓ የሚሄዱ የስደተኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም በስደት ምክንያት እያለፈ ያለ የሰው ህይወት ቁጥር ግን በንፅፅር ሲታይ አሁንም እንደጨመረ ነው።  ብዙ ስደተኞችም የተባበሩት መንግስታት በሚሰጣቸው መግለጫዎች ምክንያት ወደ ሊብያ ተመልሰዋል። .

TMP – 21/01/2019

የፎቶ መልእክት:  ከሞት የዳኑ ስደተኞች በሲ ወች 3  

ፎቶ ክሬዲት: ሲ ወች/ ትዊተር