ካሌ ለስደተኞች ምግብ እንዳሳይጥ አገደች
TMP – 11/03/2017
የፈረንሳይዋ የሰሜን የወደብ ከተማ ካልያስ በረድኤት ድርጅቶች ለስደተኞች ምግብ እንዳይከፋፈል ደነገገች፣ ድንጋጌዉ በካልያስ አዲስ የስደተኞች ካምፕ እንዳይቋቋም የሚደረግ ጥረትን የሚያግዝ ነዉም ተብሏል፡፡
ይህ የከተማዋ አስተዳደር ድንጋጌ “በመደበኛና ቋሚነት በበርካታ ግለሰቦች የሚከፋፈል ምግብ” በመጠለያ ካምፖች የስደተኞች ተደጋጋሚና ቀጣይ መሰባሰብን ለማቆም ያለመ ሲሆን ሁኔታዉ ለአካባቢዉ ጸጥታና ሰላም የስጋት ምንጭ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የከተማዋ ከንቲባ ናታሻ ቦሻርት ለስደተኞች የሚከፋፈል ምግብ ለማገድ ተጨማሪ ፖሊሲዎች ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዉ “በግሌ እንደሰዉ እንዲህ ነገር እቃወመዋለሁ” ካሉ በኃላ በከተማቸዉ ለስደተኞች የሚከፋፈለዉ ምግብ መታገድ “ይህ በቀጥታ ምግብ እንዳይከፋፈል ለማገድ ያነጣጠረሳይሆን ለከተማዋ ህግና ስርዓት እንዲሁም ጸጥታ በማረጋገጥ ለቆሻሻዎች መበራከት መንስኤ የሆነዉን የስደተኞች መሰባሰብን ለመግታት ነዉ፡” ብለዋል፡፡
ድንጋጌዉ በመጠልያ ካምፖች የሚደረጉ ሌሎች የረድኤት ስራዎችንና ምግብ ማከፋፈልን የሚከለክል ሲሆን በካምፑ ዉስጥ በቅርብ ሳምንታት ወደ ካሌ የመጡ በአብዛኛዉ ከወላጆቻቸዉ ጋር ያልተገናኙ ህጻናት የሚበዙባቸዉ 400 ስደተኞች ይገኛሉ፡፡
“ባለፉት ጥቂት ቀናት በዱናስ የኢንደስትሪ ዞን የበርካታ ግለሰቦች ስብስብ በመደበኛነት ይስተዋላል፣ ይህም ለስደተኞች በሚከፋፈለዉ ምግብ ምክንያት ነዉ” ብለዋል ከንቲባዋ በመግለጫቸዉ፡፡
“በአካባቢዉ ካሉ ሰራተኞች ፣የቢዝነስ ስዎችና ነጋዴዎች ምግብ በሚከፋፈልበት ወቅት በበጎ ፍቃደኞች በስደተኞችና በነሱ መካከል ዉጥረት ተፈጥሮ እንደነበር የሚያመለክት ቅድመ ማስጠንቀቂያ” መረጃ ደርሶኛል ሲሉም ተናግረዋል ከንቲባዋ፡፡
“ይህ ነዉ ሊፈጠር የሚችል የህዝብ መረበሽን ለመከላከል የሰዎች መሰባሰብን የሚያግድ ስርዓት ለመዘርጋት የወሰንኩት፡” ብለዋል፡፡ እገዳዉን የሚገልጹ ህጋዊ ሰነዶች በፈረሰዉ ካምፕ መለጠፋቸዉም ተገልጿል፡፡
አንድ ላለፉት አራት ወራት ለስደተኞች ምግብ ስታከፋፍል የቆየች በጎ ፍቃደኛ በማርች 2 ለ30 ህጻናት ቁርስ ለመስጠት የመጡ በጎ ፍቃደኞች ላይ ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኝ አዉራ መንገድ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ጭስ መተኮሱንም ተናግራለች፡፡
“አሁን ሁኔታዉ ለስደተኞች በጣም አስቸጋሪና ከባድ እየሆነ ነዉ መተኛትም ሆነ ገላቸዉ መታጠብ አይችሉም፣ በጣም በጣም ተዳክመዋል፣ ቀጣይ ዕድላቸዉ በእዉነት እያስጨነቀን ነዉ” ብላለች ሳራ አሮም የተባለች በጎ ፍቃደኛ፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ