በ2017 በሚዲታራንያን ባህር የሞቱ ስደተኞች ቁጥር 366 ደርሷል

TMP – 06/03/2017

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ሪፖርት ከሆነ 2017 ብቻ በሚዲትራንያን ባህር የሞቱት ስደተኞች ቁጥር 366 ደርሷል፡፡

ከነዚህ ሟቾች ቁጥር ማለትም 326 በሞት ወይም የት እንደደረሱ የማይታቁት ወይም ህልዉናቸዉ የጠፋዉ በሚድትራንያን ባህር ከሊቢያ ወደ ጣልያን በሚደረግ ጉዞ ነዉ፡፡

2016 በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረዉ 97 ስደተኞች መሞት ዘንድሮ 300% መጨመሩንም ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

በዘንድሮዉ ዓመት በሚድትራንያን ባህር በሚደረግ ጉዞ የሟቾች ቁጥር ቢጨምርም ወደ አዉሮፓ በዚህ መስመር የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር መቀነሱን የተገለጸ ሲሆን 2016 53 ቀናት ብቻ 105,427 ስደተኞች የገቡ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን ይህ አሀዝ 87% ቀንሶ 13,924 ስደተኞች ወደ አዉሮፓ መግባታቸዉ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ በዘንድሮዉ ዓመት 366 በባህር ጉዞ ላይ መሞታቸዉ የገለጸዉ ሪፖርቱ 2016 በነበረዉ 53 ቀናት ግን 425 ስደተኞች መሞታቸዉ ገልጿል፡፡ በዚህ ዓመት የሟች ቁጥር መቀነሱ በቱርክና ግሪክ መካከል የሚገኘዉ ምስራቃዊዉ የሚድትራንያን ባህር መዘጋት ዉጤት ነዉም ብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት የህገወጥ ስደተኞችን ማስተላለፊያ መስመር ከምስራቃዊዉ ሚድትራንያን ወደ መካከለኛዉ ሚድትራንያን ተቀይሮ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ለመሻገር በሚደረግ ጉዞ የህገ ወጥ ደላሎች ለስደተኞች ያላቸዉ ደንታቢስነት ተጨምሮበት የሟቾች ቁጥር መጨመሩንም ሪፖርቱ ገልጿል፡፡ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ብቃት በሌላቸዉና ከፕላስቲክና እንጨት በተሰሩ ትናንሽ ጀልባዎችን ከአቅም በላይ በመጫን የሟቾች ቁጥር እንዲጨምር ማድረጋቸዉም በተጨባጭ ተረጋግጧል ብሎል ሪፖርቱ፡፡

ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በጥር 242017 በወጣዉ ሪፖርት 2265 ስደተኞች በባህር ላይ መዳናቸዉና 136 ሬሳዎች ሲገኙ ቁጥራቸዉ ያልታወቁ ደግሞ እስከ አሁን ያሉበት እንደማይታወቅ ገልጿል፡፡