የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በ 7 ሕገ-ወጥ የሰዎች ደላሎች ይቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ
የኢትዮዽያ ፍርድ ቤቶች ኣዲስ በወጣ ሕግ በ2015 ሕገ-ወጥ የሰዎች ደላሎች ለመቅጣት ባፀደቀው መሰረት ኣሁን
ስድስት ኢትዮዽያውያንና አንድ ኤርትራውያን ተቀጥተዋል።
በዚህ ወር 7 የሕገ ወጥ የሰዎች ደላሎች ከስድስት እስከ 10 ዓመት ስለተፈረደባቸው በማረምያ ቤት ይገኛሉ። የሕገ-
ወጥ የሰዎች ደላሎች በሞት ፍርድ እንኳን ቢፈረድባቸውም ኣዲሱ ሕግ ኣላማው ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ለሚደልሉ
ለማቆም ያለመ ነው።
የቅጣት ውሳኔ የተሰጠው በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት 75 ስደተኞች በሕገ-ወጥ መንገድ
ከሱዳን ወደ ስዑድ-ኣረብ በ45000 የኣሜሪካን ዶላር በማስከፈልና፣ ሰዎቹን በመግታት፣ በመደብደብ፣ ኣስገድዶ
በመድፈር እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ኣንዲደርስባቸው በማድረጋቸው ሕገ-ወጥ ደላሎቹ ተቀጥተዋል።
ኢትዮዽያ ስደተኞች በመቀበል ከኣፍሪካ ቀዳሚ ተርታ ካላቸው ኣገሮች ኣንድዋ ነች። እንደ UNHCR ዘገባ ኢትዮዽያ
በኣሁን ሰኣት 800,000 የሚጠጉ ስደተኞች ተቀብላ ታስተናግዳለች። ሌሎች ብዙ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ደግሞ
በሱዳን ድንበር በኩል ወደ ሊብያ ወደብ ግብፅ ኣድርገው በሜድትያንያን በኩል ወደ ኣውሮፓ ሊገቡ ይሞክራሉ።
በዚህ ምክንያት ኢትዮዽያ ለሕገ-ወጥ ስደተኞች ደላሎች ማረፍያ ነች። ይሁን እንጂ የኢትዮዽያ መንግስት ለእነዚህ
የሕገ-ወጥ ስደተኞች ደላሎች በመታገል እና እንዲቆም ከ3000 ሺ በላይ በሕገ-ወጥ ደላሎች ጉዳት የደረሰባቸው
ተበዳዮች ለ69 ደላሎች 46ዎቹ በፍርድ ቤት እንዲቀጡ በማድረግ ካለፈው ኣመት የተቀጡ እንዲጨምር ኣድርገዋል።
አንደ የኣሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስራያ ቤት ዘገባ።
የሰሜን ኣፍሪካ እና የኣፍሪካ ቀብድ ባለ ስልጣኖች በሕገ-ወጥ ስደተኞች ከምንጫቸውና ዋና መተላለፊያቸው
በማጥናት የሕገ-ወጥ ስደተቶች ደላሎች መርበብ የሚበጣጥስ መርበብ በመዘርጋትና ሕግን በመደንገግ ሕገ-ወጥ
የሰዎች ዝውውር መቆጣጠር ይሞክራሉ። ከኢትዮዽያ በተጨማሪ ሱዳን በ2014 ሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር
ለመከላከል ሕግ ኣውጥታለች። ግብፅም በ2016 ሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ለማቆም ትኩረት በማድረግ ሕግ
ኣውጥታለች።
ፅሑፉን ያካፍሉ