የጣልያን ዓቃቤ ህግ የረድኤት ድርጅቶች ከህገወጥ የሰዉ ዝውውር ጋር ያላቸው ትስስር እየመረመረ ነው

የሲሲልያ ፍርድ ቤት ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሰሜን አፍሪካ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እና በሚድትራንያን የተሰማሩ ግብረሰናይ የነብስ አድን ጀልባዎች በድብቅ ስለመተባበራቸው ለማጣራት ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

በግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተሰማሩ የነብስ አድን መርከቦች ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ጀልባዎቻቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ሜድትራንያን እንዲልኩ በጥቆማ መልክ በማበረታታት ተከሰዋል፡፡ የአሁኑ ምርመራ ዋና ዓላማ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችና ግብረሰናይ ድርጅቶች በቅንጅት ህገወጥ ጉዞ ማከናወናቸዉ የሚያረጋግጥ ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ ነው ተብሏል፡፡

ዓቃብያነ ህጉ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች የነብስ አድን ጀልባዎች ስለሚገኙበት ቦታ በቂ መረጃ እንደሚያገኙ ከስድተኞች ምስክርነት ማግኘታቸውም ይገልጻሉ፡፡

ክሱን የሚመመሩት የሲሲሊያን ዓቃቤ ህግ ካርሜሎ ዙካሮ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች እና የነብስ አድን መርከቦች መረጃ እንደሚለዋወጡ አሳማኝ መረጃ መገኘቱ ገልጸዋል፡፡ ዓቃቤ ህጉ በመጋቢት 22 ሮም ውስጥ ሆኖ በሚድትራንያን ባህር የሚካሄድ የነብስ አድን ስራ የሚያስተባብረው የባህር ሃይል ማዕከል በመጥቀስ ለፓርላማ አባላት ሲናገሩ “የነብስ አድን ስራው ሁልጊዜ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ብቻ እንደማይፈጸም አምኛለሁ፡” ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ፀረ ህገወጥ የሰው ዝውውር ሶፍያ ኦፕሬሽን ኮማንደር ጣልያናዊዉ አድሚራል ኤንሪኮ ክሬዴንዲኖ በነብስ አድን ሰራተኞችና በህገወጥ አዘዋዋሪዎች መካከል ጥምረት እንዳለ ማመናቸዉ ሲናገሩ፡ “የነብስ አድን ሰራተኞች ህገወጥ አዘዋዋሪዎች በነሱ አቅጣጫ እንዲጓዙ ሆን ብለዉ ትላልቅ የመድረክ መብራቶች ያበሩላቸዋል፥” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የነብስ አድን ሰራተኞች ስደተኞች ደረጃቸው ባልተጠበቀ ትናንሽና ጥቂት እንደተጓዙ ባህር ውስጥ በሚሰጥሙ አነስተኛ ጀልባዎች በመሳፈር ህይወታቸው ለአደጋ እንዳይጋለጡ ህይወታቸውን ለማዳን ሲባል በሊቢያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ጥበቃ እንደሚያካሂዱ ይናገራሉ፡፡

በግለሰቦችና ለግብረሰናይ ድርጅቶች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች  የሚመጣ እናዳይሆን ባለስልጣናቱ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ ባለፈው ክረምት በሊቢያ የባህር ዳርቻ በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት የባህር ላይ የነብስ አድን ስራ የተካሄደ ሲሆን እነዚህም በጥርጣሬ የተያዙ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ዓቃቤ ህጉ በእነዚህ ሃገራት የነብስ አድን ስራ ሚሽኖች ምርምራ እያካሄደ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይፋዊ  ክስ አለመከፈቱም ተገልጿል፡፡ ይህ ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር የተጠረጠሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በግብር አበርነት መስራታቸዉ ከተረጋገጠ ከሰሜን አፍሪካ ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር አስተባብረዋል ተብለው እንደሚከሰሱ ተገልጿል፡፡