በምዕራባውያን የባልካን መሸጋገርያ ስደተኞች ሕገ-ወጥ ድርጊትና ጥቃት እየደረሰባቸው ነው
TMP – 23/04/2017
አዲሱ የኦክስፋም ዘገባ እንደሚስረዳው ጭካኔ የተሞላበት ድብድብና ጥቃትና ሕገ- ወጥ አያያዝ በምዕራባዊ የባልካን መሸጋገርያ እንደሚፈፀምባቸው ታውቋል፡፡
“አደገኛ ጨወታ” በተሰኘው ዘገባ እንደተመለከተው ስድተኞችን ቃለ-መጠይቅ በማድረግ በባልካን የጉዞ መስመር ለሚጠቀሙና በሰርቢያ፣ ሃንጋሪ፣ ክሮኤሽያ፣ ቡልጋርያ፡ የቀድሞ የዩጎዝላቪያ የመቄዶንያ ሪፓብሊክ በኩል የሚጓዙትን ስድተኞች በመጠየቅ ነው የተዘጋጀው፡፡
ሪፖርቱ የድንበር ባለስልጣናትን በነዛው ለስደተኞችና ህፃናት የሚያደርጉትን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ያጋልጣል፡፡ 140 ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ስድተኞች በድንበር ባለስልጣናት ብዙ እንደተሳቀዩና መንገላታት እንደደረሰባቸው በሙሉ ገልፀዋል፡፡ ባለፉባቸው ሃገራት ጥገኝነት ለመጠየቅ በሞኮሩበት ወቅት ኢሰብኣዊ አያያዝ እንደጋጣማቸው ይገልፃሉ፡፡
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው ባለስልጣናት ሰዎችን ከአንድ ሃገር ወደ ሌላ ሃገር ከሕግ ውጭ እንደሚገፉና የግለሰቦችን ጉዳይ ሳያዳምጡ፣ ሕጋዊ እገዛ ሳያደርጉና አስተርጓሚዎች ሳይመድቡና ቅሬታ እንኳን ለማቅረብ በማይመች ሁኔታ ይሸኛሉ፡፡
ይህ ዘገባ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ያወጣውን ግኝት ስድተኞች ከአንድ የአገር ግዛት አካባቢ ወደ ሌላ እንደሚባበሩ የሚገልፀውን ያጠናክራል፡፡ ለምሳሌ በሰርቢያ የስድተኞች ቡዱን የያዘ የሁለት አመት ህፃን ጨምሮ ወደ ስድተኞች መጠልያ ማእከል እየተወሰዱ እንደሆነ ነግሮአቸው ነገር ግን እልም ባለ ጫካ ውስጥና በጨለማና በብርድ በቡልጋሪያ ድንበር ጥለዋቸው ሄወደዋል፡፡
ቃለ መጠይቅ ከተደረገባቸው ሰዎች 75 ከሃንጋሪ ድንበር ወደ ሰርቢያ እንደተባረሩ፣ 19 ደግሞ ከክሮሽያ ወደ ሰርቢያ፣ 44 ከሰርቢያ ወደ ቡልጋርያ ወይም መቄዶንያ ፣ አንድ ሰው ደግሞ ከመቄዶንያ ወደ ግሪክ፣ 7 ሰዎች ከቡልጋሪያ ወደ ቱርክ እንደተባረሩ ይገልፃል፡፡ ጥቂት ሰዎች ከአንድ ግዘ በላይና ከአንድ ቦታ በላይ እንደተባረሩ ይገልፃል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ