ጀርመን በሊብያ ለሚገኙ ስደተኞች ገንዘብ ለመለገስ ቃል ገባች
ጀርመን በሊብያ የስደተኞች የማቆያ ማእከላት ለሚገኙ ስደተኞች ተጨማሪ 3.5 ሚልዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል መግባቷና ይህም ገንዘብ በሊብያ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ለሚገኙ ስደተኞች የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል እንደሚውል ታውቋል፡፡
ይህ እርዳታ ለመስጠት ያታወቀው የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሲግማር ጋብሪኤል በዚህ ወር ሊብያን በጎበኙበት ወቅት መሆኑ ታውቋል፡፡
ሚኒስተር ጋብሪኤል ከትሪፖሊ እንዳስታወቁት በሊብያ ያሉት ብዙ ስድተኞች በአሳዛኝ ሁኔታ እንደሚገኙና በ2018 ለሚከፈለው ገንዘብ ለመለገስ የተፈለገው ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ለተደረገው ይእርዳታ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ገልፃዋል፡፡ ይህንን የገንዘብ መጠን ጀርመን ከዚህ በፊት የለገሰችው የ100 ሚልዮን ዩሮ በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አማካይነት ለሚካሄደው ፕሮግራም ስራ ማስኬጃ እንደሚውል ታውቋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት ሚስተር ጋብሪኤል እንደገለፁት በሊብያ የስደተኞች ማቆያ ማእከል ያለው ሁኔታ በጣም አሳፋሪ እንደሆነና የስደተኞች የአኗኗር ሁኔታ ማሻሻል የአለም አቀፍ ማሕበረሰብ የወቅቱ አንገብጋቢ ስራ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሚኒስተር ጋብሪኤል ጨምረው እንደገለፁት በሊብያ ያሉት ተፋላሚ ወገኖች በሰላማዊ መንገድ የሰላም ጎደና እንዲከተሉና በሰላማዊ መንገድ መግባባት ላይ መድረስ እንደሚቻልና ሰላማዊ ውይይት ለዘላቂ ሰላም ብቸኛ አማራጭ መሆኑ በመጠቆም በሊብያ የፖለቲካ መረጋጋት ለማስፈንና መግባባት ላይ ለመድረስ መጣር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
“ይህንን አላማ ከግቡ ለማድረስ የሊብያ የተከፋፈሉ ሃይሎች ለሰላምና ለመደራደር ዝግጁነታቸውን ማሳየት አለባቸው፡፡ ይህም በሚደረግበት ግዜ ብቻ ነው ያለው የርስ በርስ ጦርነት ማርገብና የታሰበውን የሰላም ሁኔታ ማምጣት የሚቻለው፡፡ ህግና ሕገ መንግስታውነት የሚሰፍን፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጀርመን የገንዘብ ልገሳ ቃል የተገባው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ፊሊፖ ግራንዲ በቅርቡ በሊብያ ላደረጉት ጉብኝት ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። ግራንዲ በሊብያ ቆይታቸው ወቅት የስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ ተዘዋውረው ከጎበኙ በሃላ በስደተኞች ማቆያ ማእከላት ያሉት የስደተኞች የአኗኗር ሁኔታ በእጅጉ እንደተደናገጡና የስደተኞች የአያያዝ ሁኔታ በገንዘብ በገንዘብ እጥረት ምክንያት መሆኑ መገንዘባቸው ታውቋል፡፡ ለዚህ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወኪል በሊብያ ለሚካሄዱ ፕሮግራሞች እንደሚያግዝና እንደሚያጠናክር ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ