የአውሮፓ ህብረት ስደተኞችን መልሰው ለመቀበል በማይፈቅዱ ሀገራት ላይ የቪዛ ገደብ ሊያደርግ ነው
አውሮፓ ውስጥ ጥገኝነት የማግኘት መብት የሌላቸው ህገወጥ ስደተኞችን መልሰው ለመቀበል በማይፈቅዱ የአፍሪካና ሌሎች ሀገራት ላይ የቪዛ ገደብ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (አህ) ስምምነት ላይ ደርሷል።
የአውሮፓ ህብረት ስምምነቱ ላይ ሊደርስ የቻለው ብራስለስ ውስጥ ለሁለት ቀናት ከተደረገ ስብሰባ በኋላ ነው፤ በዚህም ስብሰባ ላይ “ከሶስተኛ ወገን ሀገራት ጋር የሚኖረውን የቪዛ ፖሊሲ መከለስን… ጨምሮ ሁሉንም አማራጭ መንገዶችን” ለመጠቀም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ወደ አውሮፓ የሚደረጉ ጉብኝቶችን መገደብ፤ ዒላማ የተደረጉት ሀገራት ባላስልጣናት ስደተኞችን መልሰው ለመቀበል እንዴት እንደሚገፋፋቸው አንድ ከፍተኛ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማት ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል: “ተመላሾችን እንዲቀበሉ ለማሳመን ቪዛን ልንጠቀምበት እንችላለን።”
አዲሱ እርምጃ በአሁኑ ሰዓት ወደ አውሮፓ የባህር ጠረፎች የሚደርሱት አብዛኞቹ ሰዎች ጥገኝነት ለማግኘት ብቁ ያልሆኑ የኢኮኖሚ ስደተኞች መሆናቸውን ከግንዛቤ ያስገባ ነው።
ጥገኝነት ለማግኘት ብቁ ያልሆኑ ህገወጥ ስደተኞችን መልሰው ለመቀበል በማይፈቅዱ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የአውሮፓ ህብረት እያደገ የመጣ ቅሬታ አሳድሯል፤ ስደተኞቹም አብዛኛውን ግዜ ተመልሰው ወደ ሀገራቸው እንዳይላኩ
ፓስፖርቶቻቸውን ከጥቅም ውጪ ያደርጋሉ። ብዙ ሰዎችን ወደ ሀገራቸው ለመላክ አውሮፓ በምታደርገው ጥረት ላይ አሁን የታቀደው የቪዛ ገደብ ከአፍሪካ ሀገራት ትብብር ሊያስገኝላት ይችላል ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል።
ፅሑፉን ያካፍሉ