ኢትዮጵያና ሰዳን ድንበራቸውን በጋራ ለመጠበቅ የሚያስላቸው ስምምነት ይፋ አደረጉ

በድንበራቸው ያለውን ህገወጥ የሰውና የዕፅ ዝውውር ለመግታት የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታ የፀጥታ ሃይሎቻቸው በድንበር አካባቢ በጋራ በጥቃት እንዲጠብቁ ተስማምተዋል፡፡

የጋራ ሃይሉ በሱዳን ሴናር ግዛትና በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ሁለቱን አገራት በሚያዋስን ድንበር፣ ህገወጥ የሰውና ዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሁከትና ህገወጥ ንግድ ለመግታት ጥበቃውን ያካሂዳል፡፡

ሱዳንና ኢትዮጵያ ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውርና ስደት ለመከላከል ከዚህ በፊት ጠንካራ ህግ ያጸደቁ ሲሆን አሁን ደግሞ ድንበራቸውን ለመጠበቅ ወደሚያስችል ተጨማሪ እርምጃ ገብተዋል፡፡ ይህ የጋራ ጥምር ሃይል በቅርቡ በአማራ ክልል በኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ፀጥታ ጉዳይ ለመነጋገር ያካሄዱት ውይይት ውጤት ነው፡፡ ይህ ስምምነት ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር የሁለቱም ሃገራት የጦር አመራሮች በድንበር አካባቢ ያለውን ህገወጥ የሰው ዝውውር ንግድና ስደት ለመከላከል ያካሄዱት ውይይት ቀጣይ እርምጃ ነው፡፡

የሴናር ግዛት የድንበር ጉዳይ ዳይሬክተር ፋዲ አልማው ላ ሞሐመድ ጥዑም የጋራ ጥበቃ ዘመቻው ዓላማ በድንበር ላይ ያለውን ሁከት ለመከላከል የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ስትራቴጅክ ጥናት ተመራማሪ የሆኑት አቶ አበበ አይነቴ “ይህ የጋራ ጥበቃ በምስራቅ አፍሪካ ያሉት ሁለት ታላላቅና ብዙ የህዝብ ቁጥር ባላቸው ሁለቱ ሃገራት ለጋራ ጥቅሞቻቸው በጋራ ለመስራት ያላቸው ፍላጎት አንድ አካል ነው ካሉ በኃላ የጋራ የድንበር ጥበቃው የሁለቱ ሃገራት ስትራቴጂያዊ ትብብርን የሚያጠናክር ነውም፡” ብለዋል፡፡