የሱዳን የፖሊስ ሃይሎች 56 እስረኞች ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ አስለቀቁ

በሚያዝያ 30 የሱዳን ፖሊስ ሃይሎች ከታጠቂ ህገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች እጅ 56 የተያዙ እስረኞች ከምስራቃዊው የሱዳን ግዛት ኤል ገዳሪፍ አስለቅቀዋል፡፡

እንደ ሜጀር ጀነራል አዲል ጀማል የገዳሪፍ የፖሊስ ሃይል ዋና አዛዥ ዘገባ እስረኞቹ በከሰላና ገዳርፍ ክፍለ ግዛቶች መካከል በሚገኘው ሰው አልባ ቤት ታጉረው የነበሩ ናቸው፡፡ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ለያንዳንዱ እስረኛ የ 3 ሺሕ ዶላር ክፍያ ይጠይቁ እንደነበር ታውቋል፡፡

ከእስር ነፃ የወጡ ስደተኞች ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ በአስቃቂ ሁኔታ ተይዘው እንደነበርና ከአንድ ወር በላይ መቆየታቸው ሲገልፁ የጤናቸው ሁኔታም በጣም የተጎሳቆሉ እንደነበሩ ነው፡፡ እስረኞችን ነፃ የማውጣት ስራም ቀጥሎ ሌላ ኦፕሬሽን በማካሄድ በሚያዝያ ወር መጨረሻ የሱዳን ፖሊስ ሃይል ሌሎች 21 እስረኞችን በማስለለቀቅ ሰባት ህገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችን አስሯል፡፡ ይህም ጥምር ፖሊስ ሃይል ከከሰላ፣ ኒው ሃይፋና ሳሕል አልቡታናን በመውረርና ድንገተኛ ፍተሻ በምስራቃዊው ሱዳን በማካሄድ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ስደተኞች በሱዳን ውስጥ ታፍነው ተወስደው የነፍስ ዋጋ እንደሚጠየቅባቸው በጣም በርካታ ናቸው፡፡  ለምሳሌ እንደ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዘገባ የፖሊስ ሃይሎች እጅግ በጣም ጥቂት የሚባሉ ቦታዎች ብቻ የሚቆጣጠሩት፤ ይህም በሊብያ ድንበር ብቻ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ስደተኞች ለመታፈንና ለብዝበዛ የተጋለጡ ናቸው፡፡

ሱዳን በቅርቡ ሕገ-ወጥ ስድተኞችንና አዘዋዋሪዎችን ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡  ይህም በቅርቡ ያፀደቀችው የፀረ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ህግን ይጨምራል፡፡ ይህም ህግ ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እስከ 20 ዓመት እስራት እንደሚያስቀጣ ታውቋል፡፡