የአፍሪካ ሕብረት ለስደት ምክንያት የሆኑትን እንዲያስወግዱ ለአባል ሃገራት ጥሪ አቅረበ

ፎቶ ፡- የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ክፍል ተጠበባቂ ዳይሬክተር ዶክተር አድምረ ካምቡድዚ ምስጋና ለአፍሪካ ህብረት
የአፍሪካ ህብረት (ኤ.ዩ) ለስደት ምክንያት መነሻ የሆትን ችግሮች በስር መሰረታቸው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እንዲያቆሙ ፣ እንዲቀረፉና በሓላፊነትና በቆራጥነት እንዲሰሩ ለእያንዳንዱ አባል ሃገራትን ጥሪ ኣቀረበ፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የድህንነት ክፍል ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶ/ር ኣድምር አምቡዲዚ እንደሚሉት የአፍሪካ መንግስታት ዜጎቻቸውን ወደ ውጭ ሃገር እንዳይሰደዱ (እንዳይሄዱ) በአገሮቻቸው ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለባቸው የግድ መሆኑ ይናገራሉ፡፡ (ተናግረዋል)
ለአንድ የጋና ሬድዮ ጣብያ እንደተናገሩት ዶ/ር ኣምቢዲዚ የአፍሪካ መንግስታት የዜጎቻቸውን ህገ ወጥ ስደት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና የባርያ ንግድን ለመከላከልና ለማስቆም በእጅጉ ገና ከወዲሁ በርትተውና በቆራጥነት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የአፍሪካ ሃገሮች ለወጣቶቻቸውን በአፍሪካ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩና ወደ ሜዲትራንያን ባህር ሄደው ከሞሞት ይልቅ በሃገሮቻቸው ያለዉን ፀጋና ሃብት እንዲያውቁ እንዲሰሩና እንዲጠቀሙበት አጥብቀው አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አምቡዲዚ እንዳሉት እኛ አፍሪካውያን ሁሉም የተፈጥሮ ሃብቶች አሉን ፣ ወጣቶቻችን ከአህጉራችን እየተሰደዱ ነው፡፡ ለምን የፖለቲካ አመራሮቹ የአፍሪካ ወጣቶች እዚሁ አገራቸው የሚደሰቱበትን (በአገሮቻቸው) የሚቆይቡትን ምቹ ሁኔታ (መደላደል)ና ስነ -ምህዳር ለመፍጠር የጎላ ሚናቸውን ስለማይወጡ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህንን አስተያየት የመጣው የአፍሪካ ስደተኞች በሊብያ ለባርነት ሲሸጡ የኢኤንኤን ዘገባ አሳየና ዓለም አቀፍ ውግዘትንና ጭሆትን ካስከተለ በኋላ መሆኑ ታውቀል፡፡ዘገባው የሚያመለክተው (የሚያሳየው)ና የሚያጋልጠው በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በጠራራ ፀሓይ (በግልፅ) ለዘመናዊ ባርነት በግልፅ ገበያ ለጨረታ ቀርበው ለእያንሳንዱ ሰው እሰከ 400 ዶላር ሲቸበችቡ ሲታዩ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡
ሊቢያ ዋና የህግ ወጥ አዘዋዋሪዎችና የስደተኞች መናሃርያ መቆያ መሆንዋና ወደ አውሮፓ ለመድረስ በሜዲትራንያን በኩል የምትመች አገር በመሆንዋ ለስደተኞች ከህግ ወጥ ደላላዎችና አዘዋዋሪዎች በአከባቢው ሚሊሻዎችና የእስርቤት ዘመበኞች የሚደርሳቸው እንግልት ሰቆቃና ስቃይ የአስገድዶ መድፈር ፣ ለእስር መዳረግ ገፈጥ ቀማሾች ናቸው፡፡
ከአውሮፓና አፍሪካ የተውጣጡ መሪዎች በቅርቡ ከሊቢያ ወደ 700000 ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የሚያስችል የአስቸኳይ እቅድ ለማውጣት እየሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡