ከኒጀር ወደ ሊብያ የሚደረግ የስደት ጉዞ ለመግታት ለአውሮፓ ህብረት ጥሪ መደረጉ ታወቀ

ከ 1,200 የሚበልጡ ከሊብያ ወደ ጣልያን ሜዲተራንያን ባህርን በማቋረጥ ላይ እንዳሉ በመሞታቸው ምክንያት የአውሮጳ ተልእኮ እንዲቋቋምና የደቡባዊ ሊብያን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲቻል ጥሪዎች እየተደረጉ ናቸው፡፡

ባለፈው ግንቦት ወር ለአውሮጳ ሕብረት ኮሚሽን በተላከ ደብዳቤ እንደተገለፀው የጣልያንና የጀርመን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተሮች ቶማስ ደ ማይዚዬርና ማርኮ ሚኒቲ እንደገለፁት “ሁላችንም በመቶዎች የሚቆጠሩትን ስድተኞችን ህይወት ለመታደግ ብዙ መስራት እንዳለብንና በህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እጅ ያሉትን ስደተኞች መታደግ ግዴታችን ነው፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በደብዳቤው “የአውሮጳ ተልእኮ በኒጀርና ሊብያ ድንበር አከባቢ በአስቸካይ መመስረት፡” እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከኒጀር ወደ ሊብያ የሚደረገው ህገ-ወጥ ጉዞ ለመግታትና ለመዝጋት በድንበሮች አከባቢ ሚኒስተሮቹ ለአካባቢው ህብረተሰብ ልማትና ዕድገት ፕሮግራም ድጋፍ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡ ሌሎች እርምጃዎችም ቴክኒካዊና ፋይናንሳዊ ድጋፍ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመዋጋት ላይ ላሉት ለሊብያ ባለስልጣናትና በተለይም በኒጀር ድንበር ላሉት ይጨምራል፡፡

ጥሪውን በመደገፍ ጀርመንና ጣልያን እንዲሁም የአውሮጳ ከፍተኛው የውጭ ጉዳይ ተወካይ ፌደሪካ ሞገሪኒ እንዳሉት የሰሜን አፍሪቃ አገሮች የድንበር አስተዳደርና ቁጥጥር መጠናከር የመደገፍ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡ የአውሮጳ የውጭ ጉዳይ ተወካይ እንዳሉት በጣልያን የሚመራ የአውሮጳ ተልእኮ እንደተቋቋመና ለጉዳይ ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የዚህ ተልእኮ አካል የሆነው የጣልያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርኮ ሚኒቲ በግንቦት ወር አራት የቅኝት ጀልባዎች ለሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እንደተሰጡ፤ ሌሎች 6 ጀልባዎች በቅርቡ እንደሚሰጡትና ይህም ህግ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት እንደሚያግዝ ታውቋል፡፡

የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ግን ጀልባዎች ጦር መሳርያ እንዲታጠቁ ይፈልጋሉ፡፡ አብዱላሂ ቶምያ ከፍተኛ የሊብያ ባህር ሃይል ሃላፊ እንደሚሉት “ጀልባዎች ለቅኝት ብቻ ልንጠቀምባቸው አንችልም፡፡ ምክንያቱም ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በእጅጉ ጦር መሳርያ ታጥቀዋል፡” ብለዋል፡፡

ጀልባዎቹ ጦር መሳርያ እንዲታጠቁ ጣልያንን ጠይቀናል፣ ከአብዮቱ በፊት ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች የጦር መሳርያ ትጥቅ አልነበራቸውም፡፡ አሁን ግን ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ጦር መሳርያ ታጥቀዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡