የከሊብያ ወደ ጣልያን በባህር በመጓዝ ላይ የነበሩ ስደተኞች ሞት
ከሊቢያ ወደ ጣልያን በባህር በመጓዝ ላይ የነበሩ 186 ህገ ወጥ ስደተኞ መሞታቸው ተገለፁ፡፡ አልጀዚራ ቴሌቪዥን ባሰራጨው ዘገባ እንደገለፀው እነዚህ ለበርካታ ወራት በተለያዩ እስር ቤቶች በአስከፊ ህይወት ውስጥ የቆዩ 190 ስደተኞች ባለፈው ዓርብ ጃንዋሪ 13,2017 እኩለ ለሊት ነበር በአነስተኛ መርከብ ቁዞ የጀመሩት፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 8 ህፃናት 60 ሴቶች እንደሚገኙባቸው የገለጸው አልጀዚራ በአጠቃላይ 160 ኤርትራውያን በጀልባዋ ውስጥ ተሳፍረው እንደነበር ተገልጻDል፡፡
ስደተኞች ለአደጋ መጋለጣቸውን አስመልክተው ከሌሊቱ 9፡30 ላይ በያዙት ተንቀሳቃሽ ስልክ በአካባቢው ለነበሩ የነብስ አድን ሰራተኞች እርዳታ ጠይቀው ከ10 ደቂቃ በኋላ ቢደርሱላቸውም በተባለው ስፍራ ባለመገኘታቸው የነብስ አድን ሰራተኞቹ ለአንድ ሰዓት ያክል ፈለጋ አካሂደው ከ3 ወንዶችና ከአንድ ሴት በቀር 186ቱ በባሕር ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠዋል፡፡
እነዚህ 190 ህገ ወጥ ስደተኞች የተሳፈሩባት ጀልባ በጣም አነስተኛና ከእንጨት የተሰራች መሆኑ የተለገፀ ሲሆን፣ ይህም በአዲሱ ዓመት 2017 ዓ.ም ያጋጠመ ከባድና አሳዛኝ አደጋ መሆኑን ገልጻDል፡፡
በተጨማሪም ጃንዋሪ 16,2017 ከሊቢያ ወደ ጣልያን የተጓዙ 4,600 እንዲሁም ጃንዋሪ 17,2017 ዓ.ም 6,000 ህገ ወጥ ስደተኞች ተከታትለው ጣልያን መግባታቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ባሰራጨው ዘገባ አመልክቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ወደ አውሮፓ በባህር በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚ ገቡ ህገ ወጥ ስደተኞችን ለመከላከል አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሃገሮች ድንበራቸው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ ህገ ወጥ ስደተኞች ያለመጠልያ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው እርጥበት አዘል ብርድና ውርጭ ህይወታቸው አስከማለፍ እየደረሱ ነው ብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጀርመን መንግሥት ወደ አገሩ የገቡ ሕገ ወጥ ስደተኞች ወደመጡበት ለመመለስ መወሰኑም አልጀዚራ በድህረ ገጹ ባሰራጨው ዘገባ ገልጸዋል፡፡ የጀርመን መንግሥት በተለያዩ ወቅቶች በሀገሩቱ ባጋጠመው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶች ከዜጎቹና ፖለቲከኞች ከፍተኛ ተቃውሞና ጫና ሲደርስበት የቆየ ሲሆን፣ አሁን ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደ መጡበት ለመመለስ ውሳኔ ላይ መድረሱን የአገሪቱ የሀገር ውስጥ ደህንነት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ