የጀርሞን መንግስት በተገን ጠያቂዎችና የስድተኞች ማባረር ጥብቅ ሕግ አወጣች

የጀርመን ፓርላማ የሃገሪቱ ተገን ጠያቂዎችና ህገ-ወጥ ስድተኞችን በሚመለከት ጥብቅ የሆነ ህግ በማፅደቅ ያልተስካላቸውን ለማባረር የሚያስችላትና ለድህንነትዋ ስጋት ናቸው ያለቻቸውን ተገን ጠያቂዎች ከሃገሯ ለማባረር ያስችላታል ተብሏል፡፡

እንደ ፓርላማው ዘገባ አዲሱ ህግ የተሻሻለው ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላታል ተብሏል፡፡ያልተሳካላቸው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ህግ-ወጥ ናቸው ተብለው ለመባረርና የድህንነት ስጋት ናቸው ተብለው ክትትል እየተደረግላቸው በእስር ቤት እንዲቆዩ ይደረጋሉ፡፡

አዲሱ ህግ የጀርመን ባለስልጣናት ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞችና ህገ-ወጥ ናቸው የተባሉትን በቀላሉ ከሃገር ለማስወጣት ትእዛዝ ለማስተላለፍ ያስችላቸዋል፡፡ የትውልድ ሃገራቸው አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ወይም ፓስፖርት ያልተሰጣቸው እንደሆነም ጭምር፡፡ ይህ እርምጃ  የተከተለው ባለፈው ዓመት በበርሊን ከተማ በክሪስማስ ገበያ ላይ ጥቃት ያደረሰው የቱኒዝያ ዜጋ ቲኒዝያ ለግለሰቡ አስፈላጊውን  የማንነት ሰነድ ባለመስጠትዋ ተከትሎ እንደሆነ ያውቋል፡፡

ከፀደቁት ህጎች አንዱ በስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች የጀርመን ፌደራል መስርያ ቤት ተገን ጠያቂዎችን በኤሌክትሮኒክ መሳርያዎች ለመከታተልና ማንነታቸውን ለማይታወቁ ለማወቅ ያስችለዋል፡፡ በጀርመን የሚገኙ ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች ማንነታቸውን በመደበቅና ያልተሳካላቸውን ተገን ጠያቂዎችና  በጀርመን ለመቆየት መብት የሌላቸው ስደተኞች እንቅስቃሴአቸው የተገደበ እንደሚሆን ነው፡፡

በተጨማሪም ተገን ጠያቂዎች ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያገኛል የሚል ተስፋ ያላቸው የጠያቂዎች ሂደት መልስ እስከሚያገኝ በመጠልያ ጣብያ እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡

የጀርመን የሃገር ውስጥ ሚኒስተር ደ ማይዚየር ለአዲሱ ህግ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቋማችን ግልፅ ነው፡፡ የኛ እርዳታና የማገናኘት ስራ የሚፈልጉ ስደተኞችና  የመፈናቀልና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማገናኘት ለሚፈልጉ  በተለይ የማጭበርበር ስራቸው ለተጋለጠባቸው ሰዎች፡፡

የውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ጨምረው እንደገለፁት የተወሰኑ ህገ-ወጥ ተገን ጠያቂዎች ሳይቀጡ ላመለጡ ስደተኞች በትክክል ተቀባያቸውን ያላስመዘገቡ ዜግነታቸው ያልገለፁት ይጨምራል፡፡