ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ተመለሱ
322 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጃንዋሪ 29 እና 30/2019 ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህ የመመለስ ስራ የተከናወነው የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም)፣ የየመን እና የኢትዮጵያ መንግስት ባደረጉት ትብብር ነው።
እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ቃል ከሆነ ከዚህ ቁጥር ሩብ የሚሆን ስደተኛ አቅም የሌላቸው ህጻናት እና ሴቶች ናቸው። በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ስር በነጻ አገልግሎት የሚንቀሳቀሱ አባላት ያደራጁዋቸው ከስደት ተመላሾች እስከ 2018 ኖቨምበር መጀመርያ ሳይመለሱ ቆይተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከ2015 ጀምሮ በየመን በተጀመረ የርበርስ ጦርነት ምክንያት ነው።
እነዚህ ስደተኞች ወደስደት የሄዱበት ምክንያት ድህነት እና የስራ ዕድል አለማግኘት ነው ተብለዋል። ከፊሎቹ ወደ ገልፍ ሀገራት ሲሄዱ ነበር የተያዙት። ከፊሎቹ ደግሞ የቀይ ባህርን ሳይሻገሩ ወደ ሰሜን በመጓዝ በግብጽ አድርገው ብሜዲትራንያን በኩል ወደ አውሮፓ ለመውጣት አልመው ሲጓዙ የነበሩ መሆናቸውን ተነግረዋል። ይሁንና እነዚህ አሁን ተመልሰው ሀገራቸው የገቡ ስደተኞች የመን ሀገር ውስጥ ባለ ግርግር ምክንያት መንገዳቸው መቀጠል አልቻሉም።
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ( IOM) እንደገለጸው በ2018 ብቻ በየመን በኩል ወደ 150,000 የሚጠጉ ስደተኞች የገቡ ሲሆን ይህ ቁጥር በተመሳሳይ አመት አውሮፓ ከደረሱ 107,000 ስደተኞች የላቀ ነው።
“ከሚመጡ ስደተኞች አብዛኛዎቹ በየመን ላይ ያለ ችግር ምን ያህል እንደሆነ መረጃ የላችውም፡ እንዲሁም በዛ በኩል ለማቋረጥ ያል ርቀት ምን ያህል እንደሆነ እውቀቱ የላቸውም። ይሄዱና ራቻሳቸውን በጦርነት በምትታመስ ሀገር ውስጥ ያገኙታል። በመሆኑም መሰረታዊ አቅርቦት ከማጣት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት እና እንግልት ይዳረጋሉ።” ብለዋል በየመን የአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም የተልእኮ መሪ ዴቪድ ዴርቲክ።
“ስደተኞች ከየመን ወደ ሀገር ቤት መመለስ የምያስችሉ ውሱን ዕድሎች ብቻ ናቸው ያሉት” ብለዋል ሃላፊው።
በሀገሪቱ ያለ የእርስ በርስ ጦርነት በተለይ በሁን ሰዓት ስደተኞች ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ አዳጋች እየሆነ መምጣቱም ተናግረዋል። የሰብአዊ እርደታ አየርሊፍት መጥተው ስደተኞችን ሲወስዱ ስደተኞቹ በጀልባ በማጓጓዝ የኤደን ገልፍ ማቋረጥ እንደተቻለ ነው አክለው የተናገሩት። ይሁን እንጂ ይህ ጉዞም የተሳካ እንዳይሆን የባህር የአየር ጠባይ የራሱ አሉታዊ ሚና እየተጫወተ ወደ አልሁዳይዳህ ወደብ እየተመለሱ እንደነበር ገልጸዋል።
ኤጀንሲው በ2019 ለ3000 በገዛ ፈቃዳቸው ለሚመለሱ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ እቅድ እንዳለው ገልጸዋል።
TMP – 15/02/2019
ፎቶ: ብምስዝላንድ/ሻተርስቶክ. በአደን-የመን ወደቦች ላይ ያሉ መርከቦች
ፅሑፉን ያካፍሉ