በኢትዮጵያ ላሉት ስደተኞች የሚሆን አዲስ የ3 ሚልዮን ዶላር ፕሮጄክት ተጀመረ

የካታር ለልማት መዋጮ (Qatar’s Fund for Development) (QFFD) ለስደተኞችና ለኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ ማኅበረሰብ ፍላጎት የሚያሟላ አዲስ ልዩ በጎ አድራጎት ፕሮግራም መጀመሩ አስታወቀ፡፡

እየተጀመረ ያለው ፕሮግራም ከአክሽን ፎር ዘ ኒዲ በኢትዮጵያ (Action for the Needy in Ethiopia) (ANE) ጋር በ3 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡

የካታር የቀይ ጨረቃ ዋና ፀሓፊ፣ ዓሊ ሓሰን አል ሓማዲ “የሚሰጠው የ3 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ የሚውለው ለመጠለያ፣ ለውሃ፣ ለአካባቢ ፅዳት፣ ለምግብና ለመተዳደርያ ድጋፍ ነው፡፡ ይህ ስጦታ በኢኮኖሚና በሰብአዊ ችግሮች በመሰቃየት ላይ ላሉት 38,000 ተጠቃሚዎችን ስቃያቸው በመቀነስ ረገድ ይረዳል፡፡” ብለዋል

ፕሮጄክቱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙት የጋምቤላና የኦሮሚያ ክልሎች ያሉት፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳንና ከሶማሊያ ለመጡት በድሃ ማኅበረሰብ የሚሰተናገዱት 800,000 ስደተኞችን ነው፡፡

ፕሮግራሙ፣ በስደተኞች ካምፕ የ768 የቤተሰብ ሽንት ቤቶችና የውሃ ጉድጓዶች ግንባታ፣ በሺ የሚቆጠሩ ለሴቶችና ልጃገረዶች የሚሆኑ የሽንት ቤት ዕቃዎች፡ የተሻሻሉ የመኖርያ ቤቶች ግንባታና የተለያዩ የትምህርትና ከማህበረሰብ ጋር የተያያዙ ችግሮች መፍታት ያጠቃልላል፡፡

የዚህ ፕሮግራም ዜና ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ እያለች የወጣ በመሆኑ፣ ወሳኝ ለውጥ የተደረገበት ሁኔታ ነው፡፡ ባለፉት ወራት አገሪቱ የስደተኞች የዜግነት ምዝገባ፣ ስደተኞች ከፍተኛ አስተዳደራዊ መግለጫዎች ማለት የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻና የፍች ከሃገሪቱ ባለሥልጣናት ፊት በመቅረብ የመመዝገብ ሥራ ጀምራለች፡፡ በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ስደተኞቹ ካካምፕ ወጥተው መኖር የሚያስችል፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ ማውታትና በቀላሉ ትምህርት ቤት ለመግባትና በአገሪቱ ሥራ ማግኘት የሚስችል ፖሊሲ አውጥታለች