የሱዳን ባለስልጣናት በሕገ-ወጥ የሰዎች ኣዟዟሪዎች የተያዙትን ስደተኞች ኣስለቀቀ

TMP – 24/02/2017

የሱዳን ባለስልጣናት በምስራቅ ሱዳን በሕገ-ወጥ የሰዎች አዟዟሪዎች ተይዘው የነበሩትን ስደተኞች እንዳስለቀቀ ኢናልታሪክ ጋዜጣ ገለፀ፡፡ 1500 የሚጠጉ የኤርትራ፣ የሶማልያና የኢትዮጵያ ስደተኞች እንደሆኑ የተነገረው ስደተኞቹ የተገኙት በገለ ድንበር በምስራቅ ሱዳን በከሰላና ገዳሪፍ ክልሎች መሃከል እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፡፡

የክልሉ የፖሊስ ቃል ኣቀባይ እንዳለው እነዚህ ሕገ-ወጥ የተያዙት  ከሰዎስቱም ኣገሮች የተውጣጡ ስደተኞች በመጥፎ ኣያያዝ ማለትም ክፍሎቹ ያለመስኰት በማድረግ በመጥፎ ሁኔታ እንዲቆዩ ተደርጎ የነበሩ ሲሆን ከዚህ ሁኔታ ለማስለቀቅ የክልሉ ፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች ተሳትፈዋል፡፡

ህይወታቸው በኣደጋና ምንም የሙቐት መቀዥቀዛ የሌለበትና ፈፅሞ ንፅህና የሌለው ኣያያዥ ተይዘው እንደነበሩ  ለማወቅ ተችለዋል፡፡

ቃል ኣቀባዩ ኣያይዘው እንደገለጡት እነዚህ ኣስኮብላዮች በኣመሪካና ኣውሮፓ ለሚገኙ የስደተኞች ቤተሰቦች በሺ የሚቆጠሩ ዶላር እየጠየቁ እንደነበሩ ለማወቅ ተችለዋል፡፡

ፖሊስ እንደገለጠው በሰዎስቱም የምስራቅ ሱዳን ክልሎች ማለትም በቀይ ባህር፣ ከሰላና ገዳሪፍ በኣሁኑ ሰዓት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠርና መረቡን ለመበጣጠስ የመጓጓዣና የኮሙኒኬሽን ኣገልግሎቶች ከነበረው በይበልጥ እያስፋፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጥር ወር የሱዳን ባለስልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ በሕገ-ወጥ አዛዋዋሪዎች ወደ ግብፅ ሲናይ ሊኮበልሉ የተገኙትን ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ችለዋል፡፡

እነዚህ የተቀናጁ ስራዎች ለመከናወን በከሰላ ክልል የሚገኙ የፖሊስ ሃይል ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂ ስልጠና እንደተሰጠ የፖሊስ ቃል ኣቀባዩ ኣብራርተዋል፡፡