የአዉሮፓ ህብረት አፍሪካ ዉስጥ ለሚቋቋም የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል

የአዉሮፓ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሰሜን አፍሪካ ለሚቋቋመዉ የስደተኞች መጠለያዎች የገንዘብ ድጋፍ

በማድረግ በግሪክና ጣልያን በኩል የሚገቡ ስደተኞችን ለመቀነስ እቅድ አውጥተዋል፡፡

የጀርመን የኣገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቶማስ ደ መይዚራ ሚኒስቴሮቹ በጥር 26፡ 2017 በማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ

አሁን እያጋጠመ ያለዉ ቀዉስ ለመግታት በሚያስችል ዉይይት ላይ እንዳሉት “አዉሮፓ ስደተኞች ወደተሻለ ቦታ

በመዉሰድ ወደ አዉሮፓ እንደማይገቡ ማረጋገጥ አለባት፡” ብለዋል።

“በህገወጥ ደላሎችና አዘዋዋሪዎች እጅ የገቡ ስደተኞች ህይወታቸውን በመታደግ ወደተሻለ ቦታ እንዲጓዙ ማድረግ

ይገባል፡ቀጥሎም ከአዉሮፓ ዉጭ የሚገኝ ደህንነታቸዉ ወደ ሚረጋገጥበት ቦታ እንዲሁም ጥበቃና ደህንነት

የሚያስፈልጋቸዉን ለይተን ወደ አዉሮፓ እንዲገቡ ማድረግ ይገባል” ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የሚመደበዉ ገንዘብ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን፣ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅትና ሌሎች

የረድኤት ድርጅቶች በመስጠት ስደተኞች በተሻለ መንገድ ደህንነታቸው ተጠብቆ የሚቆዩበት መጠለያ ዉስጥ እንዲያዙና

አዉሮፓ ከመግባታቸዉ በፊት ጉዳያቸዉ እንዲያጣሩ የሚያስችል አቅም ይፈጥርላቸዋል፡፡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶቹ

የስደተኞችን ጉዳይ ማጣራትና የጥገኝነት ጥያቄአቸዉ ተቀባይነት ያላገኙት ደግሞ ወደ መጡበት ሃገር በመመለስ ዳግም

እንዲቋቋሙ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸዉ፡፡

ይህ በሊቢያ ወይም በቱኒዚያ እንዲቋቋም የታሰበዉ የስደተኞች መጠልያ ስደተኞች ሜዲተራኒያን ባህር በመሻገር

ህይወታቸዉ አደጋ ውስጥ ከመጣላቸዉ በፊት ሃሳባቸዉ እንዲቀይሩ የሚያግዛቸዉና እንዲሁም የጥገኝነት ጥያቂያቸዉ

ዉድቅ የሆነባቸዉ ስደተኞች አዉሮፓ ዉስጥ እንዳይቆዩ የሚያደርግ ነዉ፡፡

የአዉሮፓ ህብረትና የቱርክ ስምምንትን ተከትሎ የኤጂያንና የምስራቃዊ ሜዲተራኒያን ባህር ክልል በመዘጋቱ ወደ

አዉሮፓ የሚጓዙ ስደተኞች ቁጥር ከባለፈዉ ዓመት በአስር እጅ ቀንሷል፡፡ ባለፈዉ ዓመት ጥር ወር 48,029 ስደተኞች

የገቡ ሲሆን በዘንድሮዉ ጥር ወር ግን 3829 ስደተኞች ብቻ አዉሮፓ ገብተዋል፡፡ ይህም ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር

8% ብቻ ነዉ፡፡

ይሁን እንጂ የአዉሮፓ ሃገራት አሁንም ቁጥሩን ለመቀነስ ነዉ ያቀዱት፡፡ በቫሌታ ስደተኞችን በአፍሪካ ለማቆየት

በሚያስችል እቅድ ላይ ለመወያየት የኣገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር የላከች ጀርመን የጥገኝነት ጥያቂያቸዉ ውድቅ

የተደረገባቸዉ ስደተኞች ደህንነታቸዉ እና መብታቸዉ ተጠብቆ ከሃገርዋ ለማስወጣት በመዘጋጀት ላይ መሆንዋንም

ተናግረዋል፡፡ እንግሊዝም በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኤርትራዉያን ስደተኞች ለመቀበል ነዉ ፍላጎቷ፡፡ በቅርቡም

ከኤርትራ ለሚመጡ ስደተኞች ከዚህ በፊት ትከተለዉ የነበረዉ አሰራር በመቀየር ጥገኝነት ለሚጠይቁ ኤርትራዉያን

ስደተኞች አስቸጋሪ የሚያደርግ አዲስ መመሪያ አዉጥታለች፡፡

በታህሳስ ወር ኤርትራ ዉስጥ ስላለዉ የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክተዉ ከኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ጋር

የተወያየ የሃገሪቱ ልዑክ “የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ማመን ካለብን ከዚህ ቀደም ስደተኞች ጥገኝነት

ከሚጠይቁበት ጉዳይ በተጻራሪ የተሻለ ሁኔታ ነዉ ያለዉ” ብሏል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የሊቢያን ባህር ሃይል ለማሰልጠንና ለማጠናከር 200 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት በሚዘጋጅበትና

ጣሊያንም በበኩልዋ የጥገኝነት ጥያቂያቸዉ ዉድቅ የተደረገባቸዉ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ጠንካራ አቋምና አዳዲስ

አሰራሮች በማዉጣት ከሊቢያ መንግስት በጋራ በመተባበር በህገወጥ ደላሎችና አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ለመዉሰድ

ተዘጋጅታለች፡፡