የፈረንሳይ ፓሊስ ካሌ ውስጥ የነበሩ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችና በቁጥጥር ስር አዋለ

የፈረንሳይ የድንበር ጠባቂ ፓሊስ ካሌ ከተባለች ከተማ በህገወጥ የሰው ንግድ ተሰማርተው ወደ እንግሊዝ

የሚያሻገሩ አልባናውያን አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ያዋለው በጥር 7፡ 2017 ማለዳ ላይ ነው፡፡

ፓሊሶቹ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች የነበሩበትን ሶስት ሆቴሎችን በመክበብ አራት ህገወጥ አዘዋዋሪዎችንና 10

ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

እነዚህ ህገወጥ አልባንያውያን አጨዋዋሪዎች ካሌ በተባለች ከተማ ውስጥ ሆቴል ውስጥ ተክራይተው ስደተኞች

በማቆየት ወደ እንግሊዝ በህገወጥ መንገድ በከባድ መኪኖችና ጀልባዎች ሲያሻግሩ ቆይተዋል ያለው ዘገባው ፣

ስደተኞቹ አንዴ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ ከገቡ ለባርነትና ሴተኛ አዳሪነት እንደሚዳረጉ ገለጸ፡፡

አምስት የሆቴሎቹ ባለቤቶች ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን በመደበቅና ስደተኞቹን በአስቸጋሪ አያያዝ በማኖራቸው

ምክንያት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ እነዚህ አልጀርያውያንና ፈረንሳያውያን ባለሆቴሎች በእስር ቆይተው

በቀጣይ ጥቂት ቀናት ተከሰው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

የካሌ አቃቤ ህግ ፓሰካል ማርኮንቪል እንደገለጹት ከሆነ ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ስደተኞችን ወደ እንግሊዝ

ለማሻገር ከእያንዳንዳቸው ከ5 እስከ 10 ሺ ዩሮ እንደሚቀበሉና ይህም በህገወጥ መንገድ ለመጓዝ

እንደሚጠቀሙበት የትራንስፓርት አይነት ይወሰናል ብለዋል፡፡

የድንበር ጠባቂ ፓሊሶች ህገወጦቹ በሚጠቀሙባቸው መስመሮችና እንዲሁም ወደ ደቡባዊው የእነግሊዝ

የባህር ጠረፍ የሚያሻግሩ ወደቦች ላይ ጠንከር ያለ ጥበቃና ቁጥጥር እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል፡፡