በሊብያ ስደተኞች ለተለያዩ የሆድ እቃዎች (የስውነት ክፍሎች)

ሽያጭ እንሚታደርጉ አንድ የህግ ባለሞያ ከሰሱ
ከሲኤን ኤን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አንድ ስደተኛ እንደ ባርያ እንደተሸጠ ተናግሯል፡፡
አንድ ጋናዊ የህግ ባለሞያ ለጋና አንላይን ነውስ ሳይት (የዜና ድረገፅ) እንደተገለፀው በሊብያ የባርያ ንግድ ከሰዎች በግልፅ ጨረታ ሽያጭ በላይ መሆኑና አንዳንድ ስደተኞቹ ለሆድ እቃዎች (ጉበት ፣ ኩላሊት ሌሎች አከላት) ሽያጭ እንደሚጠቀሙባቸው አሰታውቋል፡፡

በቅርቡ በሲኤንኤን የተካሄደውን የምርመራ ማጣራት ዘገባ መሰረት በባርያ ንግድ ገበያ በሊቢያ ውስጥ የአፍርካ ስደተኞች ለጨረታ ሽያጭና ለተለያዩ የሰውነት የውስጥ አከላት ሲባል ለገበያ እንዲቀርቡና …. የተባለ የህግ ባለሞያ መግለፁን ለዚህ ስራ ሲባል ሰዎች ታፍነውና አንድ ቦታ ላይ ታጉረው በቪድዮ ምስል መመልከቱንና ቢያንስ የአንድ ሰው የሰውነት የውስጥ አካላትን በማውጣት ለሽያጭ ወደ ውጭ እንደሚላኩ እማኞቹን ሰጥቷል፡፡

ሓቁ ይህ ነው ፤ ሰዎቹ የሚሸጡት ሊሰሩ ሳይሆን የውስጥ እቃዎቻቸውን በማውጣት እንደ ኩላሊት ጉበት የመሳሰሉት እጅግ ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዳላቸው ቤንስን ይናገራል፡፡ (ተናግሯል)

የሆኑ መድሃኖቶቹ ይደረግባቸውና የውስጥ አካላትቻቸውን በማውጣት ለሽያጭ እንደሚቀረቡ ነው፡፡ ይህም በርግጥ እየሆነ ያለው ነው ይህ ዓይነቱ ስራም ደግሞ የአብኣዊ መብት ጥለት ወንጀል ነው ሲሉ ቤንስን ነውዳይ ለተባለ የቴሌቭዥንብ ማሰራጫ ጣብያ ተናግሯል፡፡

የህግ ባለሞያው የአፍሪካ ሕብረት ግዚያዊ ፍርድ ቤት በማቋቃም ነገሩን (ክሱን) እንዲያጣራ አቤቱታውን አቅርቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሓፊ አንትንዮ ጉተሬዝ የባርያ ንግዱን በመቃወም ይህ ስራ የሚያስጠላና (አስቀያሚ) ስራ ነው ብለዋል፡፡ ቀጥሎም ይህ ዓይነቱ አስቀያሚ የባርያ ንግድ ስራ ሞያ ባላቸው ባለስልጣናት እንዲጣራና ወንጀሎኞቹ ወደ ህግ ፊት ቀርበው ዋጋቸው እንዲያገኙ እንዲደረግ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረትም ለስደተኞች ከለላ እንዲደረግና ህገ ወጥ አዘዋዋሪቻቸውም ወደ ህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም የሊቢያ ምክትል ጠ/ ሚኒስቴር አሕመድ መቲግ በተባበሩት መንግሰታት የሚደገፈው መንግስታቸው ይህ በኢኤንኤን የተጋለጠው የባርያ ንግድ ወንጀል እንደሚጣራ አረጋግጠዋል፡፡