ከሰሃራ በታች በህገወጥ የሰዉ ንግድ የተሰማሩ አዘዋዋሪዎች ለአቅመ ሄዋን ላልደረሱ ህጻናት የእርግዝና መከላከያ በመድሃኒት ይሰጣሉ

TMP – 20/02/2017

ከሰሃራ በታች የሚገኙ በህገወጥ የሰዉ ንግድ የተሰማሩ አዘዋዋሪዎች ለአቅመ ሄዋን ላልደረሱ ህጻናት ጎጂ የሆነ የእርግዝና መከላከያ እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡ እነዚህ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጃገረዶች በአስቸጋሪዉ ከአፍሪካ ወደ አዉሮፓ የሚያደርጉት ህገወጥ ጉዞ የተደፈሩ ናቸዉ፡፡

በጣልያንዋ የስደተኞች መግቢያ ደሴት ላምፔደዛ በሰብአዊ ዕርዳታ የተሰማሩ ድርጅቶች እንደገለጹት ከሆነ አብዛኛዎቹ በ13 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶች ለሦስት ወር የሚያገለግል የእርግዝና መከላከያ የወሰዱ ናቸዉ ፡፡

እነዚህ ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ልጃገረዶቹ ጉዞ ከመጀመራቸዉ በፊት የእርግዝና መከላከያ እንደሚሰጥዋቸዉ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶቹ ጋር የሚሰሩ ሄለን ሮድርጌዝ የተባሉ የማህጸን ሃኪም የገለጹ ሲሆን “በጉዞአቸዉ ወቅት ለወሲብ ጥቃት እንደሚጋለጡ ያዉቃሉ በዚህ ምክንያት እንዳያረግዙም ኢትዮጵያ ወይም ሱዳን ዉስጥ መድሃኒቱን ይወስዳሉ፡” ብለዋል፡፡ ዶክተር ሮድጌዝ የሚደርስባቸዉ አሳሳቢ አካል ጉዳት እንዳለ ሆኖ ጎጂ የዉስጥ የጤና ችግር ሊያስከትልባቸዉና ያለእድሜያቸዉ ላለመዉለድ ደረጃ ሊደርሱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በዶክተር ሮድሪጌዝ ምርመራ የተካሄደባቸዉ አምስት ኤርትራዉያን ሴት ልጃገረዶች ከዚህ የተነሳ የወር አበባ እንደማታይባቸዉም አረጋግጠዋል፡፡ አብዛኞቹ ህጻናት ልጃገረዶች ከኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ የመጡ ናቸዉ፡፡

ከሰሃራ በታች ወደ አዉሮፓ በህገወጥ የሚሰደዱ አፍሪካውያን ለአስገድዶ መደፈርና የሃይል የገንዘብ ክፍያ የመጋለጥ እድላቸዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ በ2016 ዓ.ም የሰብአዊ መብት ተሟጓቹ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ 75% ከሰሃራ በታች የሚመጡ አፍሪካዉያን ህገወጥ ስደተኞች ለተለያዩ አካላዊና ጾታዊ ጥቃት በህገወጥ አዘዋዋሪዎችና ነጋዴዎች አዉሮፓ ከመድረሳቸዉ በፊት ይፈጸምባቸዋል፡፡