የሱዳን መንግስት 64 ሕገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ሊብያ ሲሻገሩ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል
የሱዳን ልዩ የድጋፍ ሓይል ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማልያና የመን የመጡ 64 ሕገ-ወጥ ስደተኞች ማክሰኞ ጥር 24፡ 2017
የሊብያን በረሃ ሲያቋርጡ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንዳደረጋቸው የሱዳን ትሪብዩን ዘግበዋል፡፡
የሰሜን ዳርፉር ምክትል አስተዳደር በጋዜጣው መግለጫ እንደተናገሩት “የሱዳን ልዩ የድጋፍ ሓይል በሕገ- ወጥ ደላሎቹ
ባካሄደው ወታደራዊ ኦፕረሽን ሕገ-ወጥ ስደተኞቹ ስድስት ህፃናት፣ አስር ሴቶች እና 48 ወንዶች ያሉበት በቁጥጥር ስር
እንደዋሉ አረጋግጠዋል፡፡”
ሕገ-ወጥ ስደተኞች ለያንዳንዳቸው 4000 የአሜሪካ ዶላር ለደላሎች በመክፈል ከፖርት-ሱዳን ወደ ሰሜን ዳርፉር በሕገ-
ወጥ አዘዋዋሪዎች ተታለው እንደመጡ ለሱዳን የአገር ውስጥ ሚኒስተር ይረከባሉ፡፡
በአዋጅ መሰረት ሽብርተኝነት እና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመታገል ለማእከላይ መንግስት፣ የሱዳን ልዩ የድጋፍ ሓይል
ከአገሪቱ የፀጥታና የድህንነት ተቋም በጋራ በመሆን በሰሜን ሱዳን ምድረ በዳ አድርገው ወደ ሊብያ በሚያቋርጡ ሕገ-ወጥ
ስደተኞችና ድላሎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀጣይ ወታደራዊ ጥቃት በማድረግ ይገኛል፡፡
ከሰኔ 2016 ጀምሮ ወደ 1600 የሚጠጉ ሕገ-ወጥ ስደተኞች በሱዳን ልዩ የድጋፍ ሓይል በሱዳን ሊብያ ድንበር አከባቢ
በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ከ3 አመት በፊት ጀምሮ የሱዳን ፓርላማ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በተመለከተ ያወጣው ሕግ፤ በሕገ-ወጥ ሰዎች
ዝውውር ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያካሂዱ እስከ 20 ዓመት እስራት እንደሚቀጡ አፅድቀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ሱዳን ለሕገ-ወጥ ስደተኞች እና ሕገ-ወጥ አዛዋዋሪዎች ምቹና መተላለፍያ በመሆን ከአፍሪካ
ቀዳሚ ነች ብሎ ይገምታል፡፡ በየወሩ ከኢትዮጵያና ኤርትራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕገ-ወጥ ስደተኞች የሱዳን ድንበር
በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመግባት በሊብያና ግብፅ አድርገው ይሄዳሉ፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ