የአውረፓ ሕብረት የሊብያን የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች ለማገዝ አቀደች

ይህ እቅድ ለአውሮፓ ሕብረት የሊብያን የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች የስደተኞች ፍሰት ወደ ማልታ የሚያደርጉት ጉዞ

ለመቆጣጠር ለማገዝ የቀረበ እቅድ ነው፡፡

ስደተኞች ወደ አውሮፓ በየሚያደርጉት ጉዞ የመጀመርያ ማረፊያቸው የሆነችው ማልታ፡ የአውሮፓ ሕብረት ወቅታዊ

ፕረዚዳንትነት ይዛ ትገኛለች፡፡ በአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ ስትራስበርግ በ ጥር 18 የማልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ

ሙሰካት ለፓርላማ አባላቱ እንደገለፁት “በመጪው ክረምት አውረፓ በመካከለኛው መዲተራንያን በሚገቡ ስደተኞች

ትጥለቀለቃለች።”

“ሁሌ በአእምሮየ የሚመላለሰው የቱርክ የሰላም ድርድሩ ካልተሳካ አውረፓ ከመካከለኛ አፍሪካ በሚገቡ ስደተኞች

እንደምትጠለቀለቅ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህም የተነሳ አውረፓ የስደተኞች ቀውስ ይገጥማታል፡፡”

ይህ እቅድ የሊብያ ሓይሎች ለማሰልጠን እና ለማገዝ፤ እንዲሁም በስምምነቱ መሰረት ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕረዚዳንት

ዶናልድ ታስክ የአጭር ግዜ መፍትሔ የሚሆኑ ተብሎ የተያዘና ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞች የሊብያ ሐይሎች በቅድመ

ግንባር ሁነው ለሚሰሩት ስራ የአውሮፓ ሕብረት ጠንካራና ዘላቂ ድጋፍ እንዲሚያደርግ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልፀዋል፡፡

ኦፕረሽን ሶፍያ የአውረፓ የባሕር ሐይሎች በሜዲተራንያን ሕገ-ወጥ የሰዎች አዟዟሪዎች በሊብያ ባህር ገብተው ለማስቆም

ሕጋዊ ስምምነት የላቸውም፡፡ ስለሆነም ጆሴፍ ሙስካት የሊብያን ሐይሎች ለማገዝና ወደ ባህር ዳር ጥግ ቀርበው የሕገ-

ወጥ ኣዟዟሪዎች ጀልባዎች ማስቆም ይፈልጋሉ፡፡

ማልታ ባለፈው ኣመት የኣውሮፓ ሕብረት ከቱርኪ ጋር የደረሰው ስምምነት ከሊብያ ጋር እንዲደገም ትፈልጋለች። “ቃላቴ

ኣላሳጥርም፡፡ አንዲት አባል አገር ብቻዋን ለዚህ ማዕበል ልትቆጣጠረው፣ልትቀንሰውና እንድታስቁመው የሚታየኝ ምንም

መፍትሔ ወይ መንገድ የለም፡ የአውረፓ ሕብረት ዋና ዋናዎቹ ሐሳቦችና መርሑ አሁን እርምጃ ካልወሰድን ነገ ይለፍ ነገር

ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ” ይላሉ የማልታ ጠቅላይ ሚንስትር።

“ይህ እቅድ የታቀደው የአውረፓ ሕብረት መሪዎች በቫልታ ለካቲት 3 በሚሰበሰቡት የሚቀርብ ነው፡፡ ይህን እቅድ እንደ

እቅድ ተስማምተው ካፀደቁት፤ ያ የተባለው ድጋፍ ስልጠና እና የመደገፍ ፕሮግራም በኦፕረሽን ሶፍያ ይከናወናል፡፡

ይህ እቅድ ከሊብያ ያሉት አጎረባች አገሮች ጭምር ስምምነትና ማለትም ከቱንዝያ እና ግብፅ በመሆን ይበልጥ

እንዲጠናከርና የሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ደላሎች መረባቸው ለመበጣጠስና በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሰሜን አፍሪካ

የሚያደርጉት ኦፕረሽን እንዲቆም ያግዛል፡፡

ይህ እቅድ በድምሩ እስከ 500 ለሚደርሱ የሊብያ ወታደሮች ስልጠና እና በማድረግ፡ በዚህ መሰረት የሊብያ ሐይሎች ሕገ-

ወጥ ደላሎች በአገሪቱ የሚያደርጉት ሕገ-ወጥ ዝውውር፣ የሕገ-ወጥ መሳርያዎች ዝውውር፣ ዕፆችና ነዳጅ ዝውውር

እንዲከላከሉና እንዲያስቆሙ እንደሚያግዛቸው ተስፋ ይደረግበታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፍ የሊብያ መንግስት ወደ ነበረችበት ሰላማዊና ጠንካራ ማእከላዊ መንግስት እንድትመለስ

እየታገለ ቢሆንም፤ ተቀናቃኝ መንግስት፡ የታጠቁ አማፂዎች፣ ተቀናቃኝ ወንበዴዎች እና ኣይ.ኤስ.ኣይ.ኤስ አብዛኛው

የሊብያ ግዛት ተቆጣጥረውታል፡፡