ኢጣልያ ህገወጥ ስደትን ለመግታት የሚያስችል ስምምነት ከደቡባዊ ሊቢያ አጎራባች ሃገሮች ተፈራረመች
ኢጣልያ ስደተኞች ሊቢያ ከመድረሳቸው በፊት በቻድና በኒጀር የስደተኞች ማቆያ ካምፖችን ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ከሃገራቱ ጋር ተፈራረመች፡፡
ስምምነቱን የጣልያን፣ ሊቢያ፣ ቻድና ኒጀር የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ያደረጉት ውይይት ተከትሎ የተፈረመ ሲሆን ሃገራቱ ከሊቢያ ጋር በሚያዋስናቸው ድንበሮች ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግም ነው፡፡
ሚኒስትሮቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ከምዕራብ አፍሪካ የሚመጡ ስደተኞች ዋና መተላለፊ በሆኑት ቻድና ኒጀር የመጠለያ ካምፕ እንደሚቋቋም ገልጸዋል፡፡
በነዚህ የመጠለያ ካምፖች ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን እንደሚሰፍሩ ገልጸው በተጨማሪም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ በሚፈቅደው መሰረት በሊቢያም ተመሳሳይ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ አራቱ ሃገራት ሽብርተኝነትና ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር ለመዋጋት የተሰማሙ ሲሆን የድንበሮቻቸውን ጸጥታ ለማጠናከር የድንበር ጥበቃ ሃይሎቻቸው መረጃ እንደሚለዋወጡም ገልጸዋል፡፡ አራቱም ሃገራት በድንበሮቻቸው አካባቢ ያለው በህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር ላይ የተመሰረተ የገቢ ምንጭ ለመግታትም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ለማካሄድም ተስማምተዋል፡፡
ፅሑፉን ያካፍሉ