የአውሮፓ ህብረት በሳህል ክልል ህገወጥ ስደትንና ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ፡፡

የአውሮፓ ህብረት በምዕራብ አፍሪካ የሳህል ክልል ሽብርተኝነትና ህገወጥ የሰው ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል የ50 ሚልዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡

የገንዘብ ድጋፍ ከአምስቱ የሳህል ቡድን አባል ሃገራት ሞሪታንያ ፣ማሊ ፣ቻድ ፣ቡርኪናፋሶ እና ኒጀር ለተቋቋመው የአፍሪካ ወታደራዊ ሃይል የሚውል ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ  ከፍተኛ ተወካይ ፊደሪካ ሞግሀሪኒ በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ የገንዘብ ድጋፍን ይፍ ሲያደርጉ እንደገለጹት “የሳህል ክልል መረጋጋትና እድገት ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓም ውሳኝ ነው፡” ብለዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፍ በአፍጣኝ እንዲሚያደርስ የገለጹት ሞገሪኒ “ለሌሎች የሳህል በድን አምስት ተባበሪ አካሎችም ወደ ትክክለኛ መንገድ እንደሚያደርሳቸው ተስፋ አለኝ ›› ብለዋል፡፡ ባለፈው መጋቢት ወር የሳህል ቡድን 5 አባል ሃገራት 5,000 ወታደሮችን ያካተተ ሃይል ለማቋቋም የወሰኑ ሲሆን ይህ አዲሱ በአባል ሃገራቱን መሪዎች ይፋ የሆነ እቅዱ ግን ወደ 10,000 ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላየ ድዮፕ “የሳህል ቡድን አምስት አባል ሃገራት ከአምስት ሳምንት በፊት በሪያድ ተገናኝተው የወታደራዊ ሃይሉ ውስጥ ከ5000 ወደ 10000 ከፍ ለማድረግ አቅድዋል፣ ይህ አካባቢው ሰፊ በመሆኑ ምክንያት ያላቸውን እውነተኛ ቁርጠኝነት ያሳያል፥” ብለዋል፡፡

ከዶቸ ቬለ ሬድዬ የተገኘው ዘገባ እንዳመለከተው አዲስ ወታደራዊ ጥምረት በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ ተግባር የሚገባ ሲሆን በአካባቢው ለሚገኘው የፈረንሳይና የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስጠባቂ ሃይልን ያጎለብተዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቀደም ሲል በሳህል ክልል የሚገኙ ሃገራት ድንበር ቁጥጥር የሌለው ክፍት በመሆኑም ምክንያት ለሽብርተኝነት፣ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

አንድ በአካባቢው በድነት ቅነሳና የምግብ ዋስትና ስራ የተሰማራው ኤስ.ኦ.ኤል ሳህል የተባለ ግብር ሰናይ ድርጅት ሃላፊ “50 ሚልዮን ዩሮው የሳህል ቡድን አምስት አባል ሃገራት መከላከል በድንበሮቻቸው ምንም አይነት ክፍተት እንዳይኖር የሚያስችል ቅንጅት ለመጀመር የሚያስችል ነው፡” ብለዋል፡፡